የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ ቅሪት ፤ ክፍል አምስት
አውሮጳውያን ቅኝ ገዢዎች አፍሪቃን ከ70 ዓመታት በላይ አስተዳድረዋል። በዚህ ጊዜ ታዲያ ማህበረሰቡ ከአንዱ ቦት ተነቅለው ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ መደረግ አልያም ለዘልአለሙ እንዳይመለሱ ማድረግ ፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ማንነታቸውን እንዲያጡ እና እንዲጠፉ ተደርገዋል። በቅኝ ግዛት ዘመን ለየአካባቢው አዲስ ስም መሰየም ቀላል ይመስል ነበር። ነገር ግን እውነቱ እንደዚያ አልነበረም። ቅኝ ገዢዎች የአፍሪቃን ምድር የራሳቸው ለማድረግ የመጨረሻ ማህተማቸው ነበርቅኝ ግዛትን መታገል የአፍሪካውያን የተቃውሞ ታሪክ ነው ። የኪሊማንጃሮ ተራራ ለአካባቢው የቻጋ ምህበረሰብ የነበረው ባህላዊ ጠቀሜታ ሙሉ በሙሉ ችላ ተብሏል። ነገር ግን አውሮጳውያኑ አሳሾች በማህበረሰቡ ዘንድ እንደምልክት የሚታዩ ልዩ አካባቢዎችን እንደገና መሰየም የሚያመጣላቸውን ጠቀሜታ ጠንቅቀው ያውቃሉ ። በዚህም ራሳቸውን አዲሶቹ የአፍሪቃ ጌቶች እና ነባር አፍሪቃውያን ነዋሪዎችን ለማሰልጠን እንደመጡም ራሳቸውን ያቀርባሉ ። ከዚህ የተነሳ በአካባቢው ነዋሪዎች ይጠሩ የነበሩ መሰል አካባቢዎች ስሞች እንዳይጠሩ ብሎም በሂደት እንዲረሱ አድርጓቸዋል።#የጀርመን ቅኝ ግዛት አስከፊ ታሪክ #Shadows of German colonialism
አዘጋጅ ካይ ኔቤ
ተርጓሚ እና ተራኪ ታምራት ዲንሳ