1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአርባምንጭ መምህራን አድማ መቱ 

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 27 2011

በአርባምንጭ የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ የመቱት፤ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ላዋጡት ገንዘብ ፤ የቦንድ ሰነድም ሆነ የተመላሽ ክፍያ አንዲፈጸምላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/37kjf
Karte Äthiopien englisch

ለሕዳሴ ያዋጣነዉ ገንዘብ ቦንድ የት ደረሰ?

በአርባምጭ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ መምህራን ከባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ የሥራ ማቆም እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ መምህራኑ ወደ ሥራ ማቆም አድማ የገቡት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ላዋጡት ገንዘብ ፤ የቦንድ ሰነድም ሆነ የተመላሽ ክፍያ አንዲፈጸምላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ነው ተብሏል። በሥራ ማቆም አድማው ምክንያት በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ 10 ትምህርት ቤቶች ካለፈው ሳምንት እስከ ዛሬ ድረስ የመማር ማስተማር ስራቸውን አቋርጠዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የመምህራን ማህበር ተወካዮችን እና የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎችን ያነጋገረው የሀዋሳው ወኪላችን ዘገባ አድርሶናል፡፡


ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

አዜብ ታደሰ 
ተስፋለም ወልደየስ