1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስልጣን ሽኩቻ በፓን-አፍሪካ ምክርቤት

ቅዳሜ፣ መጋቢት 21 2016

ከብዙ ዓመታት በፊት በማላቦ የጸደቀ አዲስ ፕሮቶኮል አለ። ይህ ለፓን አፍሪቃን ምክርቤት የተሸላ ስልጣን የሚሰጥ ነው። ይሁንና አብዛኛው የአፍሪቃ ሐገሮች በየምክርቤቶቻቸው አላጸደቁትም። ስለዚህ ይህን የማላቦ ፕሮቶኮል ሊያጸድቁት ይገባል።``

https://p.dw.com/p/4eG5k
የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ በሚገኘው የሕብረቱ ጽሕፈት ቤት ሲካሄድ
የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ በሚገኘው የሕብረቱ ጽሕፈት ቤት ሲካሄድምስል Solomon Muchie/DW

የስልጣን ሽኩቻ በፓን-አፍሪካ ምክር ቤት

የፓን አፍሪካን ምክርቤት ካለበት የበጀትና የሙስና ችግር ባለፈ በውስጥ የስልቻን ሽኩቻም እየታመሰ ነው። የምክርቤቱ ፕረዚደንት ቸረምቢራ በሃገራቸው ዙምባብዌ በሚካሄደው የሃገሪቱ የምክርቤት አባልነት ምርጫ ለመወዳደር በሄዱበት ጊዜ ምክትል ፕረዚደንቱ ኢትዮጵያዊው አቶ አሸብር ጋዬ እራሳቸውን የምክርቤቱ ተጠባባቂ ፕረዚደንት አድርገው በመሾማቸው ውዝግቡን አንሮታል። 
እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ2004 የተመሰረተው የፓን አፍሪቃ ምክርቤት መቀመጫውን በደቡብ አፍሪቃ ጁሃንስበርግ ከተማ አድርጓል። ምክርቤቱ የተዋቀረው በቀጥታ በሕዝብ በተመረጡ የምክርቤት አባላት ሳይሆን እያንዳንዱ የአፍሪቃ ሕብረት አባል በሚልካቸው ከ4 እስከ 5 የሚሆኑ ተወካዮች አማካኝነት ነው።
ምክርቤቱ ካለበት የሕጋዊ ስልጣን ብቃት ማነስ በተጨማሪ በሙስናና በበጀት እጥረት ሥራውን በአግባቡ ማከነወን እንዳልቻለ ብዙዎች ይተቻሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአመራሩ የተፈጠረ የስልጣን ሽኩቻ አጀብ እያስባለ ይገኛል።የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ቸረምቢራ በሃገራቸው ዙምባብዌ በሚካሄደው የሃገሪቱ የምክርቤት አባልነት ምርጫ ለመወዳደር በሄዱበት ጊዜ ምክትል ፕረዚደንቱ ኢትዮጵያዊው አቶ አሸብር ጋዬ እራሳቸውን የምክርቤቱ ተጠባባቂ ፕረዚደንት አድርገው በመሾማቸው ውዝግቡን አንሮታል። በኢንተርናል ክራይስስ ግሩፕ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ሊዛ ሉዋ ለDW ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው ተከታዩን ብለዋል

``ከዚህ ትዕይንት ጀርባ ያለው ምን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም። ይሁንና በዋና ፕሬዚደንት ቸረምቢራና በሳቸው ሥር ባሉት ባለስልጣናት መካከል ግጭት ተፈጥሯል። ምክንያቱም ቸረምቢራ በሐምሌ  2022 የፓን አፍሪቃ ፕሬዚደንት ሆኖ ተመርጧል። ይሁንና በሃገሩ ዙምባብዌ በቀጣዩ ዓመት በነበረው ምርጫ ለመወዳደር ወደሃገሩ ሲመለስ የሱን ቦታ ሌላ ሰው ወስዶታል። የሱ ደጋፊዎች ደግሞ ይህን ተቃውሟል። ለኔ እስከገባኝ ድረስ ሽኩቻው ይሄ ነው።ከዚያም የተለያዩ ቅሬታዎች ለቀፍሪቃ ሕብረት ቀርበዋል። በመሁኑም በአለፈው ዓመት ማገባደጃ የአፍሪቃ ሕብረት ዋና ጸሐፊ ሙሳ ፋኪ ይህንና ሌሎች የፓን አፍሪቃ ችግሮችን  የሚያጣራ ግብረኃይል ወደ ጁሃንስበርግ ልኳል። ግብረኃይሉም የደረሰበት ውጤትና ምክረሐሳብ ባለፈው የካቲት ወር በአዲስ አበባ ለተሃሄደውየሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤአቅርቧል። በስብሰባውም አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ተወስኗል።``

Logo Afrikanische Union
ምስል Ludovic Marin/AFP/Getty Images


ምክርቤቱ ካሉበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንዱ የምክርቤቱ አባላት በቀጥታ በሕዝቡ የሚመረጡ አለመሆናቸው ነው። በምርጫና በስዒረ-መንግሥታት በየሃገራቱ መንግስታት ሲቀየሩ አልያም ከአፍሪቃ ሕብረት አባልነት በሚታገዱ አገሮች የተወከሉ ሰዎች በምክርቤቱ ስለማይሳተፉ ምክርቤቱ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ እንደሚቸገርም የፖለቲካ ተንታኟ ሊዛ ያስረዳሉ

``ይህ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው። ምክንያቱም የፓን አፍሪካ ምክርቤት ህጋዊ ሥልጣን የለውም እና ደግሞ በቀጥታ በሕዝብ ድምጽ የሚመረጥ አደለም። ለምሳሌ የአውሮጳ ፓርላማን ከወሰድክ በቀጥታ በየአገሮቻቸው ተመርጠው ነው የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አባል የሚሆኑት። እዚህ ግን የተለየ ነው። እያንዳንዱ የአፍሪቃ ሃገር ልኡካኖቻቸውን ነው የሚልኩት።
በዚህ ዓመት የተነሳው ትልቁ ችግር የአንዳንድ የአፍሪቃ ሃገሮች የምክር ቤቱ አባላት በየሃገሮቻቸው በተካሄዱ ምርጫዎች አልያም በመፈንቅለ መንግስት አልያም ደግሞ አገራቱ ከአፍሪቃ ሕብረት አባልነት በመታገዳቸው ምክንያት የመንግስት መቀየር አለ። ስለሆነም በዚህ ዓመት አዲስ የምክርቤቱ አባላት ምርጫ እንዲካሄድ ነው የተወሰነው። እና በዚህ ደረጃ ላይ ነው ያለነው።``

አዲስ አበባ የሚገኘው የሕብረቱ ጽሕፈት ቤት
አዲስ አበባ የሚገኘው የሕብረቱ ጽሕፈት ቤትምስል Solomon Muchie/DW

በፓንአፍሪቃ ምክርቤት የተነሳው የስልጣን ውዝግብና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት የአፍሪቃ ሕብረት በያዝነው የጎርጎሮሳውያኑ ዓመት አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ቢወስንም ሌላ ችግርም ከፊት ለፊቱ ተደቅኗል። የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሃገራት ምክርቤቱን የተሻለ ሥልጣን ይሰጠዋል ተብሎ የጸደቀውን የማላቦ ፕሮቶኮል በአብዛኛው የአፍሪቃ ሃገሮች አላጸደቁትም።

``ከብዙ ዓመታት በፊት በማላቦ የጸደቀ አዲስ ፕሮቶኮል አለ። ይህ ለፓን አፍሪቃን ምክርቤት የተሸላ ስልጣን የሚሰጥ ነው። ይሁንና አብዛኛው የአፍሪቃ ሐገሮች በየምክርቤቶቻቸው አላጸደቁትም። ስለዚህ ይህን የማላቦ ፕሮቶኮል ሊያጸድቁት ይገባል።``
የፓን አፍሪቃ ምክርቤት እንደ አውሮጳ ሕብረትና የመሳሰሉት ዞናዊ መዋቅሮች የተሻለ ስልጣንና አወቃቀር ኖሮት ከሙስናና የስልጣን ሹኩቻ ተላቆ በመጻኢ የአሕጉሪቷ እጣ ፈንታየተሻለ ሚና እንዲጫዎች የብዙዎች ተስፋ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይገልጻሉ።


ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ማንተጋፍቶት ስለሺ