1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ4ተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ድርድር መክሸፍ በኋላ ምን ይጠበቃል?

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 11 2016

አምባሰደር ስለሺ ግብጽ ከአሁን በኋላ እንደማትደራደር ማስታወቋን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አቋም «ከመደራደር ውጭ ሌላ አማራጭ የለም» የሚል ነው። አቶ ፈቂ አህመድ ብቸኛ አማራጭ ድርድር ስለሆነ መቀጠል አለበት ሲሉ ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ደግሞ ግብጽ የአስተሳሰብ ለውጥ እስካላደረገች ድረስ የሚካሄደው ድርድር ሁሉ ለይስሙላ መሆኑ አይቀርም ብለዋል

https://p.dw.com/p/4aS7v
Seleshi Bekele, Ethiopia’s Ambassador to US and Chief GERD negotiator
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ተኛ ዙር ድርድር መክሸፍ በኋላ ምን ይጠበቃል?

ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን  ካካሄዱት 4ተኛ ዙር ድርድር መክሸፍ በኋላ ምን ይጠበቃል?
ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ከታኅሳስ 7 ቀን እስከ ታኅሳስ ዘጠኝ ድረስ አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄዱት 4ተኛዙር ድርድር ያለ ውጤት ማብቃቱን ግብጽና ኢትዮጵያ አስታውቀዋል። ሦስቱ ሀገራት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ካካሄዱት ከዚህ ሳምንቱ ድርድር መክሸፍ በኋላ ምን ይጠበቃል?  


ግንባታው የዛሬ 13 ዓመት የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደመጠናቀቁ መቃረቡን መንግሥት አስታውቋል። ኢትዮጵያ እንደምትለው ከግድቡ ግንባታ አሁን ከ94 በመቶ በላይ ተጠናቋል። ይሁንና በግድቡ የውኃ አሞላል እና አስተዳደር ረገድ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር የሚካሄደው ድርድር ግን አሁንም ማብቂያ አላገኘም። የህዳሴ ግድብ ድርድር ክሽፈት፣ የግብፅ «ዛቻ»
በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ የተለያዩ ድርድሮች እንዳጋጠሙት ሁሉ በዚህ ሳምንትም አዲስ አበባ ውስጥ ለሦስት ቀናት የተካሄደው አራተኛው ዙር የሶስትዮሽ ድርድር ያለ ውጤት አብቅቷል። ድርድሩ ያለውጤት ያበቃው የውኃ አለቃቀን በሚመለከተው ስድስተኛው አንቀጽ ላይ ከግብጽ ጋር መስማማት ባለመቻሉ መሆኑን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በየካቲት 2012 ዓመተ ምኅረት
ታላቁ የህዳሴ ግድብ በየካቲት 2012 ዓመተ ምኅረት ምስል AMANUEL SILESHI/AFP/Getty Images


ድርድሩ ያለ ስምምነት ለማብቃቱ ምክንያት ስለተባለው ጉዳይ ዶቼቬለ የጠየቃቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የናይልና የመካከለኛው ምሥራቅ ሃድሮ ፖሊቲክስ የውኃ ፖለቲካ መምህር ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ይህ አዲስ ሳይሆን የቆየ ይዘት ያለው የግብጽ ፍላጎት ነው ብለዋል። የህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ተጠናቋል መባሉ እና አንደምታዉ
«ግብጾች የሚፈልጉት የውኃ ባለቤትነታችንን ፈርሙልን እና የናንተ ውኃ አጠቃቀም በኛ መልካም ፈቃድ መሆን አለበት የሚል የቆየ ይዘት አለው።በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ውኃው የጋራችን ነው። ፍትኃዊና ርእታዊ በሆነ መንገድ ውሀችንን በጋራ የምንጠቀምበትን ስርዓት ማበጀት አለብን እንጂ ውሀ የናንተ መሆኑን የምንፈርምበት አስፈላጊነትም የለውም ፤ተገቢም አይደለም ፤ነገሩም አያስኬድም በብሔራዊ ጥቅማችን አንጻር ሲባል ነው የተኖረው።»


ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የውኃ ሀብት አስተዳደር አማካሪ አቶ ፈቂ አህመድ ነጋሽ በዚህ ጉዳይ አስገዳጅነት ውስጥ መግባት አይቻልም ሲሉ ሃሳቡን ተቃውመዋል። በርሳቸው አስተያየት ይህን መሰሉ ጥያቄ ኢትዮጵያ ወደማትቀበለው የቅኝ ግዛት ውል ስምምነት ውስጥ እንድትገባም የሚያደርግ ነው።
«ዓመታዊው የውኃ አለቃቀቁ የኃይል ማመንጨቱን ኢትዮፕያ በፈለገችው ጊዜ መቀየር ትችላለች ይላል። ራሱ ሕጋዊ መሠረት አለው።አስገዳጅ ስምምነት ውስጥ ገብታለመቀየር የነርሱን ይሁንታ ይጠይቃልና ።ሌላ የቅኝ ግዛት ስምምነት ውስጥ እንድትገባ ስለሆነ የሚፈለገውይሄ ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል ምን ተቀባይነት የለውም።እና ይሄ ነው አሁን ያጋጫቸው ወይም ወደ ስምምነት እንዳይመጡ ያደረጋቸው ይሄ ነው።» 
አምባሰደር ስለሺ ግብጽ ከአሁን በኋላ እንደማትደራደር ማስታወቋን ተናግረዋል ።እርሳቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ አቋም ግን «ከመደራደር ውጭ ሌላ አማራጭ የለም» የሚል ነው። የህዳሴ ግድብ ድርድርና የኢትዮጵያ ፍላጎትበተለይ ግብጽ በድርድሩ ተጠቃሚ ናት ያሉት አቶ ፈቂ አህመድ ብቸኛ አማራጭ ድርድር ስለሆነ መቀጠል አለበት ሲሉ መክረዋል። አንድ ወገን አልሳተፍም እያለ ታዲያ ድርድሩ እንዴት ሊቀጥል ይችላል? የተባሉት አቶ ፈቂ አህመድ ወደፊት ሊደረጉ በሚችሉ ሌሎች ጥረቶች ግብጽ ወደ ድርድሩ መመለሷየሚቀር አይመስለኝም ብለዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ንግግር ሲያደርጉ
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ንግግር ሲያደርጉ ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance


«ባለፉት አስር ዓመታት እነርሱ የሚፈልጉት ነገር ካልተሳካላቸው አንደራደርም ከዚህ በኃላ በፖለቲካው በዲፕሎማሲ ነው የምንመጣው ወይንም ደግሞ የኃይል እርምጃ ነው የምንወስደው   
የሚለው ያው የተለመደ አባባላቸው ነው እና በተደጋጋሚ ረግጠው የሚወጡበት ጊዜም አለ።ግን አሁን ባሉበት ደረጃ ማሳካት ካልተቻለ በመሪዎች ደረጃ ይነጋገሩና ወደ ድርድሩ የሚመለሱበት ሁኔታ ይኖራል ወይ ካልሆነም ደግሞ ጉዳዩን እንደተለመደው ወደ ተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ይወስዱና እነርሱ ደግሞ አይመለከታቸውም። ስለዚህ  መልሰው በአፍሪቃ ኅብረት በኩል ወደዚሁ እንደሚመልሱት ይታወቃል እና ስለዚህ መምጣታቸው የሚቀር አይመስለኝም።» ኃይል ማመንጨት የጀመረዉ ህዳሴ ግድብና የአካባቢዉ ፀጥታ ሁኔታ
ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ እንደሚሉት ግን ግብጽ የሙጥኝ ያለችው የቅኝ ግዛት አቋም ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ እስካላደረገች ድረስ የሚካሄደው ድርድር ሁሉ ለይስሙላ መሆኑ አይቀርም።
« ግብጾች የሚፈልጉት ከአሁን ቀደም እንግሊዞች ከሰጡዋቸው ስምምነት በ1929 እና ከሱዳኖች ጋራ ካደረጉት ስምምነት አኳያ ውኃ የአመንጪዎች ሀብት ሳይሆን የተቀባዮች መብት ነው። ሀብታቸውም ነው እርሱ ላይ የመሠረቱትን ማናቸውንም ንብረትና ልማት የሚገዳደር ማን የውኃ አመንጪ ሀገር ሊመጣብኝ  አይችልም። የሚል እኔ እንደሚመስለኝ በትክክልም እንደደረስኩበት የተሳሳተን ሊያስ,ጽሙ የማይችሉት አቋም በሌሎችምዘንድ ተቀባይነትሊኖረው የማይችል አቋም ይዘው ስለሚጓዙ ሌላ ዙርምቢደረግ ይሄ ዓይነት የአስተሳሰብ ቀመር ካልተለወጠ ውይይትም ድርድርም የሚሳካ አይመስለኝም።»

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ