1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

90 ቀናትን በ90 ቃላት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 17 2006

በእስር ላይ የሚገኙትን የዞን ዘጠኝ ስድስት የኢንተርኔት ጸሐፍትና ሶስት ጋዜጠኞች የሚዘክር በዘጠና ቃላት የተሰኘ ዘመቻ በማህበራዊ ድረ-ገጾች በመካሄድ ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/1CiX1
Symbolbild Facebook
ምስል Reuters

«In 90 Words»በ90 ቃላት የተሰኘው ይህ ዘመቻ በፌስቡክና ትዊተር ላይ የኢንተርኔት ጸሐፍቱንና ሶስቱን ጋዜጠኞች 90 የእስር ቀናትበ90 ቃላት የሚያስታውስ ሲሆን የተጀመረው ባለፈው እሁድ ነዉ።

ስድስቱ የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ጸሐፍቱንናሶስት ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ለእስር ከተዳረጉ ዛሬ ዘጠና ቀናት ሆናቸው፡፡ ከግል ሙያቸው ጎን ለጎን በኢ-መደበኛነት በማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካኝነት ዞን ዘጠኝን ከመሰረቱት ወጣቶች መካከል በሌለችበት የተከሰሰችው ሶልያና ሽመልስ አንዷ ናት፡፡

አሁን ስድስቱ የኢንተርኔት ጸሐፍቱንና ሶስት ጋዜጠኞች በጊዜያዊነት ከነበሩበት የፖሊስ የምርመራ ክፍል ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል። የተከሳሾች የዋስትና መብት ጉዳይ በሐምሌ 28 ቀጠሮ የሚወሰን መሆኑን ጠበቃ አምሃ መኮንን ይናገራሉ።

Soziale Netzwerke
ምስል imago/Schöning

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የኢንተርኔት ጸሐፍቱን ሥራዎቻቸውን የሚዘክር በዘጠና ቃላት የተሰኘ የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡ የዘመቻው አስተባባሪ ማህሌት ሰለሞን እና ሃሳቡን በመግለፅ የሚሳተፈዉ ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ዘመቻው የኢንተርኔት ጸሐፍቱንና ጋዜጠኞቹን ለሠሩት ሥራ ለማመስገን እና ለሥራቸውም ዋጋ ለመስጠት ያለመ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ከዛሬ 90 ቀናት በፊት የታሰሩት የኢንተርኔት ጸሐፍቱንናጋዜጠኞች ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ዓለም አቀፍ ተቋማትና የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች ከፍተኛ ወቀሳ አስከትሏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የታሰሩት በሙያቸው ሳይሆን ከሽብርተኞች ጋር ባላቸው ግንኙነት ነው ማለቱ አይዘነጋም፡፡

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ