1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
Wrong language? Change it here. DW.DE has chosen አማርኛ as your language setting.
+ + + + Breaking news: Bayern Munich win Champions League, beating Dortmund 2-1 + + + +

ዶይቸ ቬለን ያድምጡ

የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ 16:00 - 17:00 የሚለውን ማገናኛ ይጫኑ። የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆም "ዝግጅት"ን በመጫን ሊገኝ ይችላል። የአማርኛ፣ የኪስዋሂሊ፣ የሀውሳ፣የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛ እና የፖርቱጊዝኛ ቋንቋ ሥርጭትን በሚተላለፍበት ጊዜ በኢንተርኔት በInternet Explorer 8 በቀጥታ ማድመጥም ይቻላል።

አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 172 26 66 944 በSMS አስተያየት ላኩልን። ባጠቃላይ በዝግጅታችን ላይ አስተያየታችሁን በኢሜይልም ልትልኩልን ትችላላችሁ።

amharic@dw.de



  • Die Kommissionschefin der Afrikanischen Union (AU), Nkosazana Dlamini-Zuma bei einem Gipfel der AU in Addis Abeba am 16.07.2012. (c) dpa - Bildfunk+++
pixel

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    አንዲት ሴት፤ በከፍተኛው የሥልጣን ሠገነት

    እጎአበ2002 እንኮሳዛናድላሚኒዙማየመጀመሪያቱአንስታይጾታየኮሚሽኑፕሬዚዳንት ይሆኑዘንድተመረጡ።ይህየአፍሪቃኅብረትእጅግከፍተኛውየሥልጣንቦታነው።የቀድሞዋየደቡብ አፍሪቃየሀገርአስተዳደርሚንስትር በአፍሪቃኅብረትአዲስ የአሠራርመንፈስ ማሥፈናቸውን ያሣለፏቸውን100 የሥልጣንቀናትየገመገሙታዛቢዎችመሥክረዋል።ግንቦት17 ቀን2005 የተለያዩ53 ሃገራትንያቀፈውድርጅትየተመሠረተበትን 50ኛዓመትያከብራል።

  • OAU- Gipfel im Mai 1963 in Addis Abeba (/AFP/Getty Images)

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    መከፋፈልን ለማስቀረት አንድነት

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ ም ሲመሠረት ያኔ ሁሉም የክፍለ-ዓለሙ 30 ው ነጻ መንግሥታት ተሳትፈው ነበረ። የፖለቲካው የጋራ ስምምነት፤ የአፍሪቃን መከፋፈል መግታት ችሏል። በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት፤ ፀረ ቅኝ አገዛዝ ንቅናቄዎች፤ በኃያላን መንግሥታት ተጽእኖ በመፍቀሬና ጸረ ምዕራብ አቋም የተከፋፈሉ ነበሩ። ቀጥሎ የሚታየው የመሪዎች ፎቶግራፍ በ 1958 ዓ ም የተነሣ ነው።

  • Der Äthiopische Kaise Haile Selassie mit Ghana Präsident Kwame Nkrumah (L) während der Gründung der OAU, STR/AFP/Getty Images

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    የ«ፓንአፍሪካኒዝም» ጠንሳሾች

    ክዋሜ ንክሩማ(በስተግራ) -የመጀመሪያው የጋና ፕሬዚዳንት ፤ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ (መኻል) ሁለቱም ግንባር ቀደም የአፍሪቃ አንድነት አባቶች የሚባሉ ናቸው። አፍሪቃ አቀፍ ኅብረት ይሉ የነበሩት ንክሩማ «የተባበሩ የአፍሪቃ ግዛቶች»ን የመመሥረት ዓላማን ነበረ የሚያራምዱት። ይህ ፤ በቅኝ ገዥዎች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ለመውሰድ፣እንዲሁም የጋራ ገበያ ለመመሥረት ይበጃል የሚል አመለካከት ነበራቸው። ይሁንና በቅርብ ነጻነታቸውን ተጎናጽፈው የነበሩት ሃገራት ያን ያህል ርቆ ለመሄድ ፍላጎቱ አልነበራቸውም።

  • Ein Banner bei einer Demonstration von schwarzen Studenten in Soweto, Südafrika, auf dem steht Der Kampf geht weiter (AP Photo)

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    የጋራው ባላንጣ፤

    ስዕል 4 የጋራው ባላንጣ፤ 16817 532 በአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት፣ እጅግ ጠቃሚውና በቂ ምክንያትም የነበረው የፖለቲካ አጀንዳ፣ ዘረኛውን የደቡብ አፍሪቃ ሥርዓት መታገል ነበር። እንዲያውም፤ ድርጅቱ ሲመሠረት በዚያው ወቅት ነው የነጻ አውጭ ኮሚቴ የተቋቋመው። እ ጎ አ ከ 1970 አንስቶ በዘረኛው የአፓርታይድ መንግሥት ላይ ይካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ይደግፍ ነበር።

  • Eine Hacke im Einsatz auf einem afrikanischen Feld.
DW/ Peter Hille

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    ለኤኮኖሚ ዕድገት አዲስ እመርታ፤

    እ ጎ አ በ 1980 የሌጎስ ተግባራዊ አቅድ በተሰኘው መርኅ፤ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት፤ ለአፍሪቃ የኤኮኖሚ ዕድገት ማንቀሳቀሻ መላውን ነበር ለማቅረብ የፈለገው። በዚያ የተደረገው ስምምነትም፤ እ ጎ አ እስከ 2000 ዓ ም፤ የጋራ ገበያ ለመመሥረት ነበረ ትኩረቱ። ይሁንና እንዲሁ አቅድ ሆኖ ነው የቀረው። እ o አ በ 1991 የቀጠለው የአቡጃ ስምምነት እ ጎ አ እስከ 2025 የአፍሪቃ የጋራ የኤኮኖሚ ማኅበር እንዲመሠረት ነው የተለመው።

  • Westsaharische Frauen in einem Flüchtlingscamp (c) dpa - Bildfunk+++

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    አከራካሪ የነጻነት ፖለቲካ፤

    የድርጅቱ መተዳደሪያ መሠረታዊ መርኅ፣ የግዛት ወሰኞች ሳይለወጡ በዚያው እንዲቆዩ ይሆናል የሚል ነው። እ ጎ አ በ 1982 ፖሊሳሪዮ፣ ያቋቋመውን ዴሞክራቲክ ዐረብ ሰሃራዊ ሪፓብሊክ የተባለውን የምዕራባዊት ሰሐራ መንግሥት የአፍሪቃ ኅብረት ተቀበለ። ሞሮኮ በዚህ ተናዳ ከአባልነት ራሷን አገለለች። እስካሁን ከድርጅቱ ራሷን ያገለለች ብቸኛይቱ አፍሪቃዊት ሀገርም ናት፣ሞሮኮ።

  • Ugandas Präsident Yoweri Museveni bei seiner ersten Kabinettssitzung 1986 OFF/AFP/Getty Images

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    ነቀፌታ በመንግሥታቱ ማኅበር ላይ

    የአፍሪቃ ኅብረት በምዕራባዊት ሰሃራ ጉዳይ በተናጠል የፖለቲካ አቋም የወሰደበት ሁኔታ ነበረ። በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት በሚለው መመሪያው፣ በሩዋንዳ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ዝም ብሎ ነበረ የተመለከተው። ምሁራን፤ በያመቱ በአዲስ አበባ ይካሄድ የነበረውን ጉባዔ የአምባገነኖች ክለብ እያሉ መዝለፍን ነበረ የሚመርጡት። አንዱ ነቃፊ የእ ጎ አ በ 1986 በዩጋንዳ ሥልጣን የጨበጡት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ነበሩ።

  • Burundische Soldaten bei der Beerdigung des Präsidenten Melchior Ndadaye, der bei einem Putsch 1993 ums Leben kam ALEXANDER JOE/AFP/Getty Images

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    የተጠሉት ወታደሮች፤

    እ ጎ አ በ 1990ኛዎቹ መግቢያ፣ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አዲስ ፖለቲካ ቀየሰ። አፍሪቃ በውስጡ ለሚፈጠሩ ውዝግቦች ራሱ መላ መሻት ፍላጎቱ መሆኑን ገለጠ። ለዚህም ተብሎ ለሰላም የሚያስገድዱ እርምጃዎች ተቀናበሩ። በቡሩንዲ ፤ እ ጎ አ በ 1996 ወታደሮች መፈንቅለ መንግሥት ሲያደርጉ፣ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት፤የእገዳ እርምጃዎችን ወሰደ። ሆኖም ሰላም ማስከበሪያው እርምጃ በገንዘብ እጦት ጭምር ደካማ ነበረ።

  • Südafrikas Flagge zwischen anderen Fahnen der AU-Mitgliedsländer im Hauptquartier in Addis Abeba Xinhua /Landov

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    ምን ያህል ጊዜ ራስን መከላከል፤

    በአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አስፈንዳቂ ደስታ የተንጸባረቀው ድርጅቱ ከተመሠረተ ከ 30 ዓመት በኋላ ፣ እ ጎ አ በ 1994 ደቡብ አፍሪቃ የድርጅቱ አዲስ አባል ስትሆን ነበረ። ባሁኑ ጊዜ ድቡብ አፍሪቃ አዲስ አበባ ውስጥ ጠቃሚ ድርሻ በማበርከት ላይ ናት። አንዳንዶች እንደሚሉት እጅግ የገዘፈ ድርሻ ነው ያላት።

  • Gaddafi bei einem AU-Gipfel 2006.

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    የአዲስ ዘመን ጅምር፤

    በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ፍጻሜ ደቡብ አፍሪቃ፣ ከዘር አድልዎው ሥርዓት (አፓርታይድ) ከተላቀቀች በተለይም እ ጎ አ ከ 1999 አንስቶ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አዲስ እንቅሥቃሴ ተንጸባርቆበታል። የሊቢያው መሪ ሙኧመር ጋዳፊ፤ (እዚህ ላይ በ 2006 በተካሄደ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ነው የሚታዩት)አፍሪቃ አቀፍ ንቅናቄ (ፓን አፍሪካኒዝም ) የተሰኘውን «የተባበሩት የአፍሪቃ ግዛቶች» መንፈስ አነቃቅተው ነፍስ ሊዘሩበት ሞክረው ነበር። በነበራቸው ሀብት በመጠቀም ነበረ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የፈለጉት። ለብዙ አገሮችም የአባልነት ክፍያቸውን ጋዳፊ ነበሩ የሚሸፍኑላቸው።

  • Zulu Tänzer bei der Gründungszeremie der AU in Durban, Südafrika 2002 ALEXANDER JOE/AFP/Getty Images

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    ከ አ አ ድ ወደ አ ኅ፣

    ጋዳፊ የሆነው ሆኖ አልተሳካላቸውም። እንዲያውም እቅዳቸው ድርጅቱ በደርባን ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ፤ የአፍሪቃ ኅብረት ሲባል አባላቱ በሀሳብ ከሁለት እንዲከፈሉ አድርጎ ነበር ። የአፍሪቃ ኅብረት ሲመሠረት፤ በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለው የፖለቲካ መርኅ እንደገና አንሠራራ። ኅብረቱ ሲመሠረት የነበረው ስብሰባ--

  • Nelson Mandela überreicht ein Bild mit einem Emblem des Panafrikanischen Parlaments im Jahr 2006 FATI MOALUSI/AFP/Getty Images

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    አቅም የለሽ ተቋም

    የአፍሪቃ ኅብረት መዋቅሩ የአውሮፓውን ኅብረት የተከተለ ነው። አፍሪቃ አቀፍ ፓርላማ እንዲመሠረትም ነበረ ያኔ የተወሰነው። እ ጎ አ በ 2004 ከ 47 አገሮች የተውጣጡ 235 ተወካዮች ተመደቡ። የፓርላማ ተወካዮቹ አዳራሽ የሚገኘው ሚድራንድ በተባለችው የደቡብ አፍሪቃ ንዑስ ከተማ ነው። አዲስ አበባ ከሚገኘው ከማዕከላዊው የአፍሪቃ ኅብረት መ/ቤት መራቁም ፤ የሚያመላክተው፤ የፓርላማ አባላቱ የፖለቲካ ተጽእኖ ማሣረፍ እንደሚቻላቸው ነው።

  • AU-Soldaten in Darfur . (AP Photo/Jose Cendon)

    የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትና የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመት

    አዲስ እርምጃ ለሰላም

    በአዲሱ ምዕተ ዓመት 20 ከመቶው አፍሪቃውያን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የኃይል እርምጃ ያጀባቸው ውዝግቦች ህይወታቸው በመነካቱ፤ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም ማሥፈን ለሚቻልበት ተግባር ዐቢይ ትርጉም ሰጥቶታል። እ ጎ አ በ 2004 የሰላምና ጸጥታ ም/ቤት ያቋቋመውም ለዚህ ነው። ጣልቃ ገብቶ መላ የሚሻ ኃይል መላክም ተፈላጊ ሆኖ ተገኘ። በዚያው ዓመትመ ነበረ የአፍሪቃ ኅብረት፣ ለሱዳኑ የዳርፉር ክፍለ ሀገር ህዝብ ደኅንነት የራሱን ሰላም አስከባሪ ጦር ኃይል የላከው።


    አዘጋጅ: Maja Braun | ዋና አዘጋጅ: Ludger Schadomsky

አስተያየትዎ