1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳይ ወታደሮች ቅሌት በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 23 2007

ከአንድ ዓመት በፊት በቀድሞዋ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ መንስኤ በተከተለው የሃይማኖት ግጭት በተቀሰቀሰው ሁከት በርካቶች ሲገደሉ ብዙዎች ተሰደዋል።

https://p.dw.com/p/1FIsC
Frankreich Militär in der Zentralafrikanischen Republik
ምስል Miguel Medina/AFP/Getty Images



በወቅቱ ፈረንሳይ ቀድማ ወታደሮችዋን በመላክ ሃገሪቱን ለማረጋጋት አስተዋፅኦ ማድረጓ ይታወሳል። ካለፈው መስከረም ወዲህ ደግሞ የአፍሪቃ ሰላም አስከባሪ ኃይል የፈረንሳይ ወታደሮችን በመተካት ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ከገባ ወዲህ 2 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችዋን ከሃገሪቱ ማስወጣት ጀምራለች። በጎርጎሮሳዊው ታህሳስ 2013 እስከ ሰኔ 2014 መካከል በሃገሪቱ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ተሰማርተው ከነበሩት የፈረንሳይ ወታደሮች አንዳንዶቹ በታዳጊ ወጣቶች ላይ የወሲብ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚያጋልጥ ዘገባ ይፋ ከተደረገ በኋላ ጉዳዩ ማነጋገሩ ቀጥሏል።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ