1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዓቀፍ ለኢትዮጵያውያን ትብብር ልገሳ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 25 2006

የትብብሩ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ ማህበሩ የጀመረው የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ በተቀናጀ መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል ።

https://p.dw.com/p/1AksM
Saudi Arabien Riad Unruhen
ምስል AFP/Getty Images

በሳውዲ አረቢያ ስቃይና እንግልት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለመታደግ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፍ ትብብር የመጀመሪያ የገንዘብ ድጋፍ ለዓለም ዓቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም በእንግሊዘኛው ምህፃር IOM ዛሬ አስረከበ ። የትብብሩ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ ማህበሩ የጀመረው የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ በተቀናጀ መልኩ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል ። የገንዘብ ድጋፉን የተረከበው የዓለም ዓቀፉ የስደተኞች መርጃ ተቋም የውጭ ግንኙነት ሃላፊ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የማቋቋሙን ተግባር ለመቀጠል መጠነ ሰፊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል ።

አበበ ፈለቀ

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ