1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዋንጫው ማጣሪያና ኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ሰኔ 10 2005

የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን በመጪው 2014 ዓ-ም ብራዚል ውስጥ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር ለመድረስ በሚደረገው የአፍሪቃ ማጣሪያ ትናንት ደቡብ አፍሪቃን 2-1 በማሸነፍ የምድቡን አንደኝነት ማረጋገጡ አይዘነጋም።

https://p.dw.com/p/18rGA
ምስል DW

ይሁንና የዓለም እግር ኳስ ፌደሬሺኖች ማሕበር ፊፋ ቡድኑ ከሣምንት በፊት ቦትሱዋና ውስጥ ባደረገው ግጥሚያ አንድ ያልተፈቀደለት ተጫዋቹን ሳያሰልፍ አልቀረም ሲል ዛሬ በከፈተው ምርመራ መልሶ ሶሥት ነጥቦች እንዳያጣ እያሰጋው ነው። እርግጥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተሸናፊ ተደርጎ ቢፈረድበትም ምድቡን በሁለት ነጥቦች ልዩነት መምራቱን የሚቀጥል ሲሆን ከማዕከላዊት አፍሪቃ ሬፑብሊክ ጋር በሚያካሂደው የምድብ-አንድ መጨረሻ ግጥሚያ አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር የማለፍ ትልቅ ዕድል አለው። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መቀጣት ደቡብ አፍሪቃን እንደገና ከሞት የሚመልስ ነው የሚሆነው። በጉዳዩ ዛሬ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አቶ ሰውነት ቢሻውን በስልክ አነጋግረናል፤ ያድምጡ!

መሥፍን መኮንን

አርያም ተክሌ