1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከርሰ ምድር እምቅ ኃይል ምንድን ነዉ?

ረቡዕ፣ ጥቅምት 27 2006

ባለፈዉ ሰሞን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን ከአንድ የዉጭ ኩባንያ ጋር ከከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል ለማመንጨት እና ከእንፋሎት የሚገኝን የኤሌትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል ተስማምቷል። የመሬት ዉስጥ የእንፋሎት ኃይል ምንጭ ምንድን ነዉ?

https://p.dw.com/p/1ADEG
ADVANCE FOR USE SUNDAY, AUG. 28, 2011 AND THEREAFTER - In this July 28, 2011 photo, giant ducts carry superheated steam from within a volcanic field to the turbines at Reykjavik Energy's Hellisheidi geothermal power plant in Iceland. Scientists in the CarbFix experiment will separate carbon dioxide from the steam and pump it underground to react with porous basalt rock, forming limestone, to see how well the gas most responsible for global warming can be locked away in harmless form. (Foto:Brennan Linsley/AP/dapd)
ምስል AP

በዕለቱ ጥንቅራችን ከከርሰ ምድር ስለሚወጣዉ የእንፋሎት ኃይልና ኢትዮጵያ ስላላት የእንፋሎት ኃይል ክምችት ይቃኛል። ኢትዮጵያ ከሬይክያቪክ ጂዖ-ተርማል ኩባንያ ጋር የተፈራረመችዉ ዉል የመጀመርያ የግል ኤሌትሪክ አመንጭ ኩባንያ መሆኑ ተነግሮአል። በኢትዮጵያ ኮርቬቲ የእንፋሎት ማመንጫ ፕሮጄ በስምንት ዓመት ዉስጥ 1000 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ ባለሞያዎቹ ከወዲሁ ተናግረዋል። ጂኦተርማል ምንድነዉ? ከከርሰ ምድር ይገኛል የሚባለዉ እምቅ የእንፋሎት ኃይልስ በምን ምክንያት ይፈጠራል? በኢትዮጵያ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የጆኦተርማል ጥናት ዳሪክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ከበደ የኢትዮጵያ የከርሰ ምድር የእንፋሎት ኃይል ከዚህ ቀደም እንደተጠቀሰዉ መጠን ሳይሆን፤ በቅርቡ ይፋ በወጣ መረጃ መሠረት እጅግ ብዙ የኃይል ክምችት እንዳላት ያስረዳሉ። ከከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል ለማመንፀት ከሪኪያቪክ ጋር ስምምነት ሲደረግ ተሳታፊ የነበሩት በኢትዮጵያ የዉሃና የኢነርጂ ሚ/ር የኃይል ጥናት፣ ልማትና ክትትል ዳይሬክተር እንዲሁም በኢትዮጵያ የኤሌትሪክ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል፤ አቶ ጎሳዬ መንግሥቴ ፤ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የከርሰ ምድር የእንፋሎት ኃይል እጅግ በጥቂቱ ጥቅም ላይ ዉሎአል፤

Grafik: Erdwärme für die Messerstadt Riem
ምስል Stadtwerken München SVM

የዓለም የጆኦተርማል ጥናት እንደሚያመለክተዉ ይላሉ፤ በጂኦተርማል ጥናት የከፍተኛ ትምህታቸዉን ያጠናቀቁት አቶ ሰለሞን ከበደ ሆነ፤ በኢትዮጵያ የዉሃና የኢነርጂ ሚ/ር የኃይል ጥናት፣ ልማትና ክትትል ዳይሬክተር እንዲሁም በኢትዮጵያ የኤሌትሪክ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል፤ አቶ ጎሳዬ መንግሥቴ፣ በዓለማችን ዙርያ ከፍተኛዉን የከርሰ ምድር እንፋሎት ተጠቃሚ ሀገር ዩናይትድ ስቴትስ ፤ ስትሆን በመቀጠል ኤንዶኜዥያ፤ አይስላንድ፤ ቱርክ፤ ኤልሳልቫዶር፤ ኢጣልያ ፤ እንዲሁም ኬንያ እያለ በቅድም ተከተል ይቀጥላል። ኬንያ ግን በአፍሪቃችን ቀደምትዋ የከርሰ ምድር ሙቀት ኃይል ተጠቃሚ ሀገር ናት። በከርሰ ምድር ሙቀት ኃይል አጠቃቀም ላይ ለቃለ ምልልስ የተባበሩንን እያመሰገንን ሙሉዉን ጥንቅር የድምጽ ማድመጫዉን በመጫን እንዲያደምጡ እንጋብዛለን!

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ