1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዉን ስደተኞች መከራ

ዓርብ፣ መጋቢት 27 2005

ጩኸቱ ይቀጥላል። ከኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ፥ ወገኖቻቸዉን ለአደን ባሕር-አሳ-አዞ ገብረዉ ቀይ ባሕርን የተሻገሩ ኢትዮጵያዉያንን ስቃይ-ሰቆቃ እንስማ።የመን።ከሰነዓ እንጀምር።

https://p.dw.com/p/18AAN
Refugees sit outside in an open area as there is lack of tents at the Dollo Ado refugee camp, Ethiopia, Thursday, July 7, 2011. The worst drought in the Horn of Africa has sparked a severe food crisis and high malnutrition rates, with parts of Kenya and Somalia experiencing pre-famine conditions, the United Nations has said. More than 10 million people are now affected in drought-stricken areas of Djibouti, Ethiopia, Kenya, Somalia and Uganda and the situation is deteriorating, (AP Photo/ Luc van Kemenade)
ምስል AP

የመን የሚገኙ ኢትዮጵያዉን ስደተኞች የሚደርስባቸዉ ግፍና በደል ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ዓለም አቀፉ የሥደተኞች መርጃ ድርጅት (IOM) አስታወቀ።ዓለም አቀፉ ድርጅት እንደሚለዉ በተለይ የመንን ከስዑዲ አረቢያ ጋር በሚያዋስነዉ አካባቢ የሠፈሩ ሥደተኞች ከምግብና መጠለያ ችግር ባለፍ በወረቦሎች እየታገቱ የሚደርስባቸዉ ግፍ ከሚነገረዉ በላይ ነዉ።በኢትዮጵያ የIOM የመገናኛ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ደምሰዉ ብዙወርቅ እንደሚሉት መሥሪያ ቤታቸዉ ሥደተኞቹን ለመርዳት ቢሞክርም በገንዘብ እጥረትና በስደተኞቹ ቁጥር መብዛት ምክንያት ተፈላጊዉን ርዳታ መስጠት አልቻለም።


ትናንት ሱዳን የገቡ የኢትዮጵያ በጣሙን ደግሞ የኤርትራ ስደተኞችን ሥቃይ ሰቆቃ ሰምተን ነበር።ወደ ሰሜን አፍሪቃ-እስከ ሊቢያ፥ ሽቅብ ወደ ሰሜን እስከ ሜድትራኒያን ማዶ እስከ ሞልታ ወይም ኢጣሊያ፥ ደግሞ በተቃራኒዉ ቁል ቁል ወደ ደቡባዊ አፍሪቃ እስከ ታንዛኒያ፥ ማላዊ፥ ሞዛምቢክ ወይም ደቡብ አፍሪቃ ጥግ እሕ-ቢሉ የኢትዮጵያ፥ የኤርትራ፥ የሶማሌ ስደቶችን ስቃይ ሰቆቃ-እስኪያንገሸግሽዎት ይሰማሉ።

ጩኸቱ ይቀጥላል። ከኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ፥ ወገኖቻቸዉን ለአደን ባሕር-አሳ-አዞ ገብረዉ ቀይ ባሕርን የተሻገሩ ኢትዮጵያዉያንን ስቃይ-ሰቆቃ እንስማ።የመን።ከሰነዓ እንጀምር።

ብዙ ጊዜ የተገለጠዉ ብዙ ችግር፥-የመኖሪያ ፍቃድ አያገኙም።ሥራ የላቸዉም።ሥራ ካገኙም አንዳድ አሰሪዎች ይደበቧቸዋል። ክፉዎቹ ይደፍሯቸዋል።ደሞዝ ሳይሰጡ የሚያብሯቸዉም ብዙ ናቸዉ።ሳዑዲ አረቢያ ጥግ ሐራጥ በምትባለዉ ከተማ ካሉት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ፥ የሰነአዎቹ ችግር-ሴትዋ ራሳዋቸዉ እንደሚሉት ቅንጦት ብጤ ነዉ።

ሴትዮዋ ከሩቅ ያዩ-የሰሙትን ነገሩን፥-እሱ ደግሞ እዚያዉ ነዉ።ሐራጥ።ይኸኛዉ ከኢትዮጵያ ከመሰደዱም በፊት ጋዜጠኛ ነበር።እዚያም ሔዶ የሙያ ልክፉቱ አለቀቀዉም። ጉዳተኞች አሉበት እየሔደ ሲችል እርዳታ፥ ይጠይቅላቸዋል። ሲያቅተዉ በደላቸዉን ለሌሎች ያሳዉቃል።አይቷል ሰምቷልም።

ግፉ ልክ የለዉም፥ ገፈኞቹ ግን ሰለቦቹ እንደመሰከሩ ከሩቅ ያለነዉ እንደምን ሰማዉ ወይም ዓለም አቀፉ መገናኛ ዘዴዎች እግረ-መንገዳቸዉን እንደሚነግሩን አይደለም።

ስደተኞቹ እንደሚሉት ካለሙት ሳዑዲ አረቢያ ወይም ሌሎች የፋርስ ባሕረ-ሠላጤ አካባቢ ሐገራት መግባት የማይማቻል ነገር ነዉ።እዚያዉ የመን መቆየትም የመደብደቢያ፥ መቆረጪያ፥ መደፈሪያ ቀንን መጠበቅ ነዉ።ወደ ሐገር የሚመልሳቸዉም የለም።የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲማ «አሳፋሪ» ይለዋል ጋዜጠኛዉ

በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የአይ ኦ ኤም የመገናኛ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ደምሰዉ ብዙ ወርቅ እንደሚሉት የስደተኛዉን ሥቃይ መከራ መስሪያ ቤታቸዉ ያዉቀዋል።

ለመርዳትም ይፈልጋል፥ ይሞክራልም።ሁሉንም ችግረኛ ለመርዳት ግን ገንዘብ የለም።

ሥቃይ ሰቆቃዉ ቀጥሏል።መፍትሔዉ፥ ላሁኑ አይታወቅም።

Karte des Jemen mit den Nachbarländern Saudi Arabien Oman Somalia und dem Golf von Aden
ምስል DW
People walk past destroyed houses in what used to be the center of the city of Zalambessa, Ethiopia, on the border with Eritrea, in this file picture taken on Friday, Nov. 11, 2004. The city was almost entirely destroyed during the last war with Eritrea and most of its inhabitants still live in dire conditions in tents provided by the Red Cross or in destroyed houses. Ethiopia expressed concern Tuesday after the U.N. announced it was pulling peacekeepers out of almost half their border posts along the border that separates Ethiopian and Eritrean armies. (AP Photo/Boris Heger)
ምስል AP

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ


ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ