1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ፓርላማ ልዑካን በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 10 2005

ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ።

https://p.dw.com/p/199rb
ምስል Solomon Mengist

ኢትዮጵያን ለ3 ቀናት የጎበኘው የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብት ልዑካን ቡድን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የተያዙበትን እስርቤት እንዳይጎበኝ ተከለለ ። ከአዲስ አበባ የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ቡድኑ እስር ቤቱን እንዲጎበኝ ፈቃድ አግኝቶ ነበር ። የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የታሰሩትን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈታ ጠይቋል ።
በጀርመን የአረንጓዴ ፓርቲ አባልና የአውሮፓ ፓርላማ የሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ወ/ት ባርባራ ሎህቢላር የተመራው ይኽው የልዑካን ቡድን ከትናንት በስተያ እሰከዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ከአፍሪቃ ህብረት ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፓርላማው አፈ ጉባኤ እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጋር በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ተወያይቷል ።
በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ እንዳነጋገረ አለ። በኢትዮጵያ የሚሆነው ነገር ሁሉ በውጭ መንግሥታት ዐይንም ያታያል።

Straßburg Europäisches Parlament
የሽትራስቡርጉ የአውሮፓ ፓርላማምስል picture-alliance/dpa

በመሆኑም፤ የአውሮፓ ፓርላማ የሰብአዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ፤ በጀርመናዊቷ ባልደረባቸው ባርብራ ሎህቢለር መሪነት አዲስ አበባ ውስጥ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግሯል። ሎህቢለር፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በኤኮኖሚ፤ ማኅበራዊ ኑሮ፣ ባህል፣ በተለይ ትምህርትን በመሳሰሉት መሻሻል መታየቱን ተገንዝበናል ነው ያሉት። አዎንታዊ ያልሆነውን ገጽ ስንመረምር ፣ብዙዎቹ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች በተለይ በልማትና ሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ ያተኮሩት ፣ አሳሪ በሆነ ድንጋጌ ፍጹም መሥራት በማይቻልበት ሁኔታ መገፋታቸውን ለመመሥከር ችለናል ብለዋል። ደንቡን ይለውጡት ዘንድ ለባለሥልጣናቱ ነግረናቸዋል። ከሰብአዊ መብት ኮሚሽኑም ጋር ተነጋግረናል። ግን ነጻ መሆኑ አጠያያቂ ነው። ነጻው መገናኛ ብዙኀን፣ችግር እንዳጋጠመው ነው። የመንግሥትን አመራር ዘይቤ ለሚተቹ ጋዜጠኞችም አደጋ አለው። የተለያዩ ሥርጭቶችን ፣ የ DW ን መታፈን ጭምር አንስተን ተነጋግረናል።
ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ። እንዲሁም ፍጹም ፍትሃዊ ያልሆነ የፍርድ ቤት ምርመራ ተካሂዶ እሥራት የተበየነባቸው ዜጎችም እንዲለቀቁ መጠየቃቸውን ነው የጠቆሙት ። በውይይቱ ወቅት ባለሥልጣናት ስለ ህገ መንግሥት ባያወሱም አከራካሪው ነጥብ ምን እንደነበረ ባራባራ ሎህቢለር ገልፀዋል


«ጥያቄው እና የሐሳብ ልዩነት ያለን ከአንዳንድ የህገ-መንግሥቱ አንቀጾች አተረጓጓም(በተግባር የማዋል ጉዳይ ነው ። እነርሱ የመንግሥት ስላልሆኑ ድርጅቶች ሲወሳ ሐቀኛ ነፃ ድርጅቶች አይደሉም ። በህብረተሰቡ ውስጥ አክራሪ አመለካከት ከሚያራምዱ ጋር ግንኙነት ያላቸው በመሆናቸው እንታገላቸዋለን ነው ያሉት ። ከሲብሉ ማህበረሰብ ጋር በዛ ያሉ ስብሰባዎች ማድረግ ችለናል እነርሱም ያደረግነውን ዓይነት ጉብኝት እንድንገፋበትና የኢትዮጵያን ጉዳይ ተመልሰን ለአውሮፓ ህብረትና በአጠቃላይ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እንድናሳውቅ ጠይቀውናል ። »
የተቃውሞ ፓርቲ ደጋፊዎች ለሠላማዊ ሠልፍ ሲዘጋጁ የማዋከብ እርምጃ እንደሚወሰድ እንቅፋትም እንደሚያጋጥማቸው ሲናገሩ ተሰምቷል ። ያም ሆኖ በሳምንቱ ማለቂያ ላይ ሰልፋቸውን አካሂደዋል ። ይህ መንግሥት የዴሞክራሲውን በር ገርበብ ማድረጉን የሚያሳይ ወይስ የማስመሰል ተግባር ነው ? ከርስዎ ግንዛቤ በመነሳት ምን ይላሉ ?
« የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሰዎች በራሪ ወረቀቶችን በማሰራጨታቸው አርባው ተይዘው መታሠራቸው ተነግሯል እርግጥ ነው መንግሥት በር ለመክፈት ትንሽ ገርበብ ማድረጉ አዎንታዊ እርምጃ ነው ነገር ግን እንደ ሰብዓዊ መብት ፖለቲከኛ ህጎች የተጣሱበትንና አዎንታዊነት የማይታይባቸውን ሂደቶች ልብ ብለህ ታስተውላለህ። ከዚህ በተጨማሪ ሳልጠቅስ የማላልፈው ጉዳይ ያነጋገርናቸው በሰብዓዊ መብት ዙሪያ የሚሠሩ ሰዎችና ለዚህ መብት የሚታገሉት ወገኖች እንዳሉት ሁኔታው በርግጥ የበር መከፈትን ሳይሆን የበር መዘጋትን ሁኔታ ነው የሚያሳየው ። »

Menschenrechten eine Stimme geben
ባርብራ ኦኽቢለር


ምዕራባውያን መንግሥታት የልማት እርዳታን ከመልካም አስተዳደር ከፕሬስ ነፃነት ከህግ የበላይነትና ከዴሞክራሲ ጋር ለማቆራኘት ፍላጎት እንዳላቸው ቢገልጹም ተግባራዊ ሲሆን አልታየም ። ፀረ-ሽብር የተሰኘው አዋጅ የመንግሥት ባልሆኑ ድርጅቶች የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር ማድረጉ በፕሬስ ነፃነትም ላይ ብርቱ እርምጃ መወሰዱ እንደቀጠለ መሆኑ ይነገራልና ፣ የጀርመንና የአውሮፓ ህብረት የልማት እርዳታ እንዳለፈው ጊዜ ሁሉ አሁንም ያለ አንዳች ሳንክ ይቀጥላል ይላሉ ?
«የኔ ተስፋ ፖለቲከኞቹ ሁሉ በልማት ዘርፍ የሚሰሩትን የሰብዓዊ መብትን ይዞታ ሳያገናዝቡ ተግባራቸውን እንደማያከናውኑ ነው ። የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻል አጥብቀው መጠየቅ ይኖርባቸዋል። በትምሕርት በባህልና በመሳሰሉት አስመስጋኝ ተግባር ፈጽመዋል ላሏቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጠቃሚ የሚሰኙ መልዕክቶችን ሳያስተላልፉ አልነበረም የልዑካኑ ቡድን አባላት ውይይታቸውን የደመደሙት ።
«መልዕክታችን በተጨማሪ ፀረ ሽብር ህጉን ፣ የፀጥታ ስጋት ያልሆኑ በዛ ያሉ ሂስ አቅርቢ ሰዎችን እየያዛችሁ ለማሰር አታውሉት ። የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች ትርጉም ያለው ሥራ እንዳያከናውኑ የሚገታውን መመሪያ ደንብም አንሱት ። በመጨረሻም የጠየቅነው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ በማሳየታቸው ብቻ ወይም በአንድ መልክ ወይ በሌላ መንግሥትን በመተቸታቸው የታሰሩትን ሰዎች በነፃ እንዲለቋቸው ነው ።»

African Union, Addis Abeba, Äthiopien
የአፍሪቃ ኅብረትምስል DW

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ