1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተንቀሳቃሽ ስልክ 40ኛ ዓመት

ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2005

እ ጎ አ በ 1875፣ የድምጽ ሞገድ በሽቦ ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ተለውጦ እንዲተላለፍና ፤ ምልክቱ፤ በድምፅ ፤ በቃላት እንዲሰማ ያበቃውን ፤ ስልክ የተባለውን መሣሪያ ፣አለክሳንደር ግርሃም ቤል ከሠራ ወዲህ፤እ ጎ አ በ 1876 በተሽከርካሪ « ዲስክ»

https://p.dw.com/p/1895z
የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ ስልክምስል picture-alliance/dpa

እ ጎ አ በ 1875፣ የድምጽ ሞገድ በሽቦ ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ተለውጦ እንዲተላለፍና ፤ ምልክቱ፤ በድምፅ ፤ በቃላት እንዲሰማ ያበቃውን ፤ ስልክ የተባለውን መሣሪያ ፣አለክሳንደር ግርሃም ቤል ከሠራ ወዲህ፤እ ጎ አ በ 1876 በተሽከርካሪ « ዲስክ» ላይ በኤሌክትሪክ ርዳታ፣ ምስል ማሳየት እንደሚቻል ጀርመናዊው Paul Gottlieb Nipkow ካሳወቀና እስኮትላንዳዊው ጆን ሎጊ ቤርድ፣ ራሱ በተናጠል ባካሄደው ተመሳሳይ ምርምር የቴሌቭዥንን ምሥጢር ለህዝብ ካሳዬ በኋላ፣በሩሲያዊ አሜሪካዊው ቭላዲሚር ዝቮሪኪን ፣ እ ጎ በ 1933 ኛዎቹ ዓመታት ፤ በ 1940ኛዎቹ ዓመታት ይበልጥ እስኪሻሻል ድረስ፤ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች እንዲሠራጩ ለማድረግ ማብቃቱ ተረጋገጠ። በኋላም እንደገና BAIRD ባለቀለም ምስሎችን በቴሌቭዥን ማሠራጨት የሚቻልበትን አብነት አግኝቶ ማሠራጨት እንደሚቻል

Motorola RAZR
ሞቶሮላ RAZRምስል Getty Images

ካመላከበት ዘመን አንስቶ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ በመስታውት ሣጥን የሚታይበት አስደናቂ የሥነ ቴክኒክ ግኝት በዓለም ውስጥ መዛመቱ አልቀረም። ከዚያም የኮምፒዩተር ዘመን ከተተካ በኋላ፤ ውሎ አድሮ ፤ መዳፍ በሚያክል የሥነ ቴክኒክ ውጤት ያለሽቦ ድምጽንም ምስልንም የሚያቀብሉም የሚያሠራጩም መሣሪያዎች ቀርበዋል። በአሁኑ ጊዜ አገልግሎታቸው የተራቀቀና የተለያየ ይሁን እንጂ ፤ የዚህ ብርቅ ድንቅ አገልግሎት ሀ ብሎ የተጀመረው ልክ ከ ዛሬ 40 ዓመት በፊት እ ጎ አ ሚያዝያ 3 ቀን 1973 ዓ ም ነው። ጀማሪዎቹ፣ ከቺካጎ ፣ኢሊኖይ፤ ዩናይትድ እስቴትስ፤ የሞቶሮላ ሽቦ የለሽ ስልኮች ሥነ ቴክኒክ ኢንጂኔሮችና የአዲስ ግኝት ባለቤቶች ዶ/ር ማርቲን ኩፐርና ጆን ኤፍ ሚቼል ናቸው። Dyna TAC(Dynamic Adaptive Total Area Coverage)የተባለው ከአንድ ኪሎ በታች ይመዝን የነበረው ሽቦ የለሽ ስልክ ለናሙና ከቀረበ በኋላ በ 10ኛው ዓመት ነበረ ለገበያ የቀረበው።ብርቅ ድንቅ ሆኖ ብቻ አልነበረም የታየው ዋጋውም በጣም ውድ ነበረ! ፤ 4,000 የአሜሪካ ዶላር!

Indien Mädchen Kind Handy Mobiltelefon Handyverbot
ምስል picture alliance/Dinodia Photo Library


ሱሪ ኪስ ውስጥ የምትያዘው ንዑሷ የእጅ ስልክ ገበያ ላይ የዋለችው፣ እ ጎ አ በ 1989 ዓ ም ነበረ። « ማይክሮ ታክ » የሞቶሮላ የአጅ ስልክ ንዑስ ብቻ አይደለም የመጀመሪያይቱ ታጣፊ የእጅ ስልክ ነበረች። ከዚያ በኋላም ነበረ አነስ ያሉም ሆኖም የተራቀቁ የእጅ ስልኮችን ማቅረብ ዘመናዊ ፈሊጥ እየሆነ የመጣው። በ 1992 የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ሞቃት ወራት ዲጂታል የእጅ ስልኮች ተተኪዎች ሆነው ቀረቡ። በ 1994 በእጅ ስልክ አጫጭር የጽሑፍ መልእክቶች (SMS)ማስተላለፍ ተጀመረ። በ 1997 የሚታጠፉ፤ የሚንሸራተቱ ፣ የእጅ ስልኮች ዓይነቱን አበዙት።
ሥነ ቴክኒኩ ተራመደ። በእጅ ስልክ (ሞባይል) Mp3-Player,Radio,እንዲሁም የቪዲዮ አገልግሎት መደበኛ እየሆነ መጣ። ለ WAP (Wireless Application Protocol)እና ለ GPRS (General Packet Radio Service) ምሥጋና ይግባቸውና፣ ተጠቃሚዎች፤ የኢንተርኔት ድረ ገጾችን መጎብኘት ችለዋል። ቴሌቭዥን፣ በእጅ ስልክ የሚታይበት ጊዜም ሩቅ እንደማይሆን ነው የሚነገረው።

Nokia Mobiltelefon
የኖክያ ሞባይሎችምስል picture-alliance/dpa


እ ጎ አ በ 2007 Apple በጣት የሚዳሰሰውን የመጀመሪያውን iPhone ለገበያ ሲያቀርብ ብርቅ ድንቅ ተባለ። የመጀመሪያው «ስማርትፎን» አልነበረም፤ ግን ለተጠቃሚዎች አመቺ ሆኖ በመቅረቡ ተወደደ። በኋላም ፤ ለ 3ኛ ጊዜ ተሻሽሎ ከተሠራው(3G) ከ 2001 አንስቶ ይቀርብ ከነበረው የሥነ ቴክኒክ ውጤት ጋር የሚስማማ ሆኖ ተገኘ።
LTE(Long Term Evolution) በተሰኘው በረጅም ጊዜው ዝግመታዊ ለውጥ፤ እጅግ ዘመናዊ ከሆኑ የእጅ ስልኮች የተራቀቀ ተግባር በ 4ኛው የማሻሻያ ምዕራፍ የሚጠበቀው፤ መኖሪያ ቤቶችን አውቶሞቢሊችንና መ/ቤቶችን ማጠላለፍ ሳይሆን አይቀርም። የተራቀቁ የእጅ ስልኮች አዲስ ሥራ ገና አልተገታም፤ በዐይን እንቅሥቃሴ የሚታዘዙ የእጅ ስልኮችም በመሠራት ላይ
ናቸው። በአሁኑ ጊዜ በአለም ውስጥ 6 ቢሊዮን ገደማ ተንቀሳቃሽ ስልኮች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ