1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብርትልስማን የዓለም የዲሞክራሲ ይዞታ ዘገባ

ሐሙስ፣ ጥር 15 2006

በዓለማችን ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄድ በርካታ ህዝባዊ አመፅች መታየቱ እየተበራከተ መትዋል። በሰሜናዊ አፍሪቃ፤ በዩክሪይን፤ በታይላንድ በየቀኑ አመፅ የቀላቀለ ህዝባዊ ተቃዉሞ የእዕለት ዕለት ክስተት ሆንዋል።

https://p.dw.com/p/1AwHe
Transformationsindex 2014 (BTI) der Bertelsmann Stiftung
ምስል DW/K. Gomes

ብሪትልስማን የተሰኘዉ የዓለም ሀገራትን የዲሞክራሲ ይዞታ የሚያጠናዉ ድርጅት ይፋ ባደረገዉ ጥናት መሰረት በዓለማችን የሚካሄደዉ ህዝባዊ አመፅ እየሰፋ ይሄዳል እንጂ አይቀንስም።ስለ ብሪትልስማን ጥናት ሆወልሃንስ ክርስቲና የዘገበችዉን አዜብ ታደሰ አጠር አድርጋ አሰባስባዋለች።
በቱኒዝያ የተቀጣጠለዉ ህዝባዊ አብዮት በተለያዩ ሀገራት ተሰራጭቶ ቀጥሎአል። በአሁኑ ወቅት ህዝባዊ አመፅ፤ በተለያዩ ዓለም የመገናኛ ብዙሃን በእለቱ የሚቀርብ ዋንኛም ርዕስም ሆንዋል። ብሪትልስማን የተሰኘዉ የሀገራት ዲሞክራሲ ይዞታ ተንታኙ ድርጅት፤ በተለያዩ የዓለማችን በተለያዩ ክፍሎች የሚካሄደዉን ህዝባዊ አብዮት ግምግሞ፤ በቅርቡ ባወጣዉ መግለጫ፤ አመፁ በመቀጠል የሚሰፋ እንጂ የሚያቆም አለመሆኑን አስታዉቋል። በድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ምሁርዋ ሃዉከ ሃርትማን ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት ፤ በቀጣይ ዓመታት ይህ ህዝባዊ አመፅ ተጠናክሮ ይቀጥላል
« ወደፊት በሌሎች ሀገራት ከስር የሚቀሰቀስ አመፅ አለ የሚል ግምት አለን። በተጨማሪ ህዝቡ እርስ በርስ በቀላሉ ለመገናኘት እና ሃሳብ ለመለዋወጥ፤ ሚዲያን በመጠቀም መንገድ ይፈልጋል። በዶሞክራስያዊ መንገድ የተመረጡ መንግስታትም ቢሆን፤ የህዝቡን የመጻፍና የመናገር መብት በመገደብ፤ የብዙሃን መገናኛ ላይ፤ መርማሪ በማቆም ያጣራሉ። በጎአ 2010 ዓ,ም በአረቡ አብዮት እንደተደረገዉ ሁሉ ቱዩ-ተርና እና ዩ-ቲዩብን በመጠቀም እንቅስቃሴዎችን ማራመድ ይቻላል። ልክ አሁን ኪይቭ እና ባንኮክ ላይ እንደሚታየዉ አይነት ህዝባዊ አብዮት ማለት ነዉ። ይህ አይነቱ አመፅ አሁን ያልተጠበቀ ጉዳይ ሳይሆን እተለመደ መጥቶአል»
የብሪትልስማን ምሁራን፤ በማደግ እና በፈጣን ለዉጥ ላይ በሚገኙ 129 የዓለም ሀገራት ዉስጥ፤ ለጥናታቸዉ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አቅርበዉ፤ የጥናቱን መዘርዝር ይፋ አድርጓል። ከመካከላቸዉ ለምሳሌ በሀገራቱ ዉስጥ ነጻ ምርጫ ስለመደረጉ፤ ሃሳብን በነጻነት የመናገር መብት ስለመኖሩ፤ ባጠቃላይ የሰብዓዊ መብት ስለመከበሩ፤ የተነሱ ጥያቄዎች ይገኙበታል። በሌላ በኩል ጥናቱ የማህበራዊ ኑሮ ስልት እና የኤኮኖሚ አደረጃጀት እንዲሁም ሙስናን ለመግታት ስለሚደረጉ ጥረቶች ም ይቃኛል። በጥናቱ ዉስጥ ዴሞክራሲ በሚለዉ ርዕስ ስር ፤ የኢኮኖሚ ግብይትና የአስተዳደር ጥራት ተቀምጠዋል። በጥናቱ ዉጤት መሰረት አዎንታዊ እድገት ካሳዩት የመጀመርያዎቹ ዓለም ሃገራት ዝርዝር ዉስጥ ለምሳሌ ሃንጋሪ ፤ ኢስላንድ እና ታይዋን ይገኙበታል። በእድገት መዘርዘሩ አሉታዊ ዉጤት ካገኙት የመጨረሻዎቹ ሀገሮች መካከል ሶርያ፤ ማሊ፤ የመን እና ሱዳን ተቀምጠዋል። በድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ምሁሩ ሃዉከ ሃርትማን ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት፤ ባሳለፍነዉ የጎ,ዓ በዓለማችን በርካታ አመፅ ቢታይም ካሳለፍነዉ ዓመታት የዲሞክራሲዉ ይዞታ አልተሻሻለም፤
«ምንም እንኳ በበርካታ ሀገራት አመፅ ቢካሄድም የተለወጠ ነገር አልታየም። በሀገራቱ ዉስጥ በጎርጎረሳዉያኑ 2012 ዓም ከነበረዉ የዲሞክራሲ ይዞታ ጋር ሲወዳደር ምንም የተሻሻለ ነገር አላየንም። የአረቡ አብዮት ከጀመረ በኃላ በአኃዝ ሊታይ የሚችል ለዉጥ ይኖራል የሚል ግምት ነበር። በመጀመርያ በቱኒዝያ ከዝያም በጎረቤት በሚገኙ አረብ ሀገራት አመፆች ተካሂደዋል፤ አመፁ ማንያምር እና ምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ቀጥሎ የዴሞክራሲ ተስፋ ሰቶ ነበር»
እንደ ድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ምሁር ሃዉከ ሃርትማን በሩስያ በስሪላንካ፤ በሰሜን አፍሪቃ የሚታየዉ የፖለቲካ ዉጥረት መፍትሄ እንዳያገኝ ተደርጓል። በዓለም የሚታየዉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ታፍኖአል። እንዲያም ሆኖ አመጽ መታየቱ ይቀጥላል

Veranstaltung: Tyrannei der Mehrheit?
ምስል DW
Secrets of Transformation Grafik Bertelsmann Stiftung

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ