1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩሲያና የዩናይትድ ስቴትስ ዉዝግብ

ዓርብ፣ የካቲት 28 2006

ሩሲያ ጦሯን ክሬሚያ ግዛት አስፍራለች በማለት የምትወነጅለዉ ዩናይትድ ስቴትስ ለጦሩ መሥፈር ተጠያቂ ባለቻቸዉ በሩሲያና በክሬሚያ ግዛት ባለሥልጣናት ላይ ገንዘብ የማንቀሳቀስና የጉዞ ማዕቀብ ለመጣል መዘጋጀቷን አስታወቃለች።

https://p.dw.com/p/1BM0Q
ምስል picture-alliance/dpa

ሩሲያና ምዕራባዉያኑ ሐገራት ዩክሬንን በተለይም የክሬሚያ ግዛትን በበላይነት ለመቆጣጠር የገጠሙት እሰጥ አገባ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ዉዝግቡን ለማርገብ የዩናይትድ ስቴትስ እና የሩሲያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በአካል፥የሁለቱ ሐገራት መሪዎች በሥልክ ያደረጉት ዉይይትም ከአግባቢ ዉጤት ላይ አልደረሰም።ሩሲያ ጦሯን ክሬሚያ ግዛት አስፍራለች በማለት የምትወነጅለዉ ዩናይትድ ስቴትስ ለጦሩ መሥፈር ተጠያቂ ባለቻቸዉ በሩሲያና በክሬሚያ ግዛት ባለሥልጣናት ላይ ገንዘብ የማንቀሳቀስና የጉዞ ማዕቀብ ለመጣል መዘጋጀቷን አስታወቃለች።የክሬሚያ ምክር ቤት የግዛቲቱ ሕዝብ ግዛቲቱ ከሩሲያ ጋር ዳግም እንድትቀየጥ ወይም ከዩክሬን ጋር እንድትቆይ በድምፁ (በሪፈረንደም) እንዲወስን መወሰኑንም ዩናይትድ ስቴትስ ሕገ-ወጥ ብላዋለች።ዉዝግቡንና የዩናይትድ ስቴትስን አቋም በተመለከተ የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ