1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ታይምስ መፅሄት መታገዱ

ሰኞ፣ ጥር 27 2005

አቶ ተመስገን ለእገዳው የተሰጡትን ምክንያቶች መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሏል ። ዶቼቬለ ስለ አዲስ ታይምስ መፅሄት እገዳ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲን አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

https://p.dw.com/p/17Xxo
Titel: Temesgen Desalegne(Eine der bekanntesten Journalisten der freie Presse und Editor von "Addis Times"in Addis Abeba,Ähiopien Schlagworte: Druck auf Pressefreiheit Fotograf : DW/Yohannes Gebreegziabher
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝምስል DW



በየ 2 ሳምንቱ 35 ሺህ ቅጂ ይታተም የነበረው አዲስ ታይምስ መፅሄት መታገዱን የመፅሄቱ ባለቤት አስታወቀ ። የአዲስ ታይምስ ባለቤት ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ለዶቼቬለ እንደተናገረው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ 3 ምክንያቶችን ዘርዝሮ መፅሄቱን አግዷል ። አቶ ተመስገን ለእገዳው የተሰጡትን ምክንያቶች መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሏል ። ዶቼቬለ ስለ አዲስ ታይምስ መፅሄት እገዳ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲን አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ