የብሪታንያው የራዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት-ቢቢሲ- ባለፉት ወራት ፣ ህጻናት ለአያሌ ዓመታት ፣ የወሲባዊ ጥቃት ዒላማዎች ሆነው ፤ ዜናው ተደብቋል በሚል ወቀሳና ክስ ሲታመስ ቆይቷል።
የብሪታንያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ቢቢሲ አንድ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ወግ አጥባቂ እንደራሴ አንድ ግለሰብን በወሲብ ደፍረዋል ሲል ከአሥር ቀን በፊት ባስተላለፈው የተሳሳተ ዜና ሰበብ በገጠመው ቅሌት የተነሳ የቢቢሲ ዋና ኃላፊ ጆርጅ ኤንትዊስል ከሁለት ወራት በፊት የያዙትን ስልጣናቸውን መልቀቃቸው የሚታወስ ነው።
« ባለፉት ጥቂት ሣምንታት የተከሰተው ሁኔታ ቢቢሲ አዲስ መሪ መሰየም አለበት የሚለው ውሳኔ ላይ እንድደርስ ገፋፍቶኛል። » ቲም ዴቪስ አሁን ቢቢሲን በተጠባባቂ ዋና ኃላፊነት እንዲያስተዳድሩ ተሰይመዋል።
በሀሰት የተወነጀሉት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴ ወቀሳውን ሀሰት ሲሉ ካስተባበሉ በኋላ ወቀሳውን የሰነዘረው ግለሰብም እንደራሴውን በስህተት መወንጀሉን አምኖዋል። የታወቀው ሟቹ የቢቢሲ የቴሌቪዝን አስተዋዋቂ ጂሚ ሳቪል ለብዙ ዓመታት በመቶ የሚቆጠሩ ሕፃናትን በወሲብ ደፍሮዋል በሚል ከተወነጀለ ወዲህ ብዙ ወቀሳ ሲፈራረቅባቸው የቆዩትና ስልጣናቸውን የለቀቁት ኤንትዊስል አሁን 563,000 ዩሮ ማካካሻ ይከፈላቸው መባሉን ወግ አጥባቂ የምክር ቤት እንደራሴዎች ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ ነቅፈዋል።
ኤንትዊስል ስራቸውን ከለቀቁ በኋላ የዜና ክፍል ኃላፊ ሄለን ቦደን እና ምክትላቸው ስቲቭ ሚቼል ትናንት ከስራ ቦታቸው ለጊዜው መታገዳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። ሁለቱ ግለሰቦች ሳቪል ሕፃናትን መድፈሩን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች ባለፈው ዓመ በተደጋጋሚ ቢደርሱዋቸውም ዘገባዎቹን ለማቅረብ ያልፈለጉበት ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ ከስራ ቦታቸው እንዲርቁ ታዘዋል።
ይህን ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ የለንደንዋነ ዘጋቢአችን ሐና ደምሴን በስልክ አነጋግሬአታለሁ።
ሐና ደምሴ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሀመድ