1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቋንቋና ባህልን ማወቅ

ሐሙስ፣ መስከረም 16 2006

ከሀገር ርቀዉ፤ በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሀገራቸዉን ቋንቋ ባህልና የማንነታቸዉን መለያ ለልጆቻቸዉ እንዴት እና በምን ዘዴ ያወርሳሉ?

https://p.dw.com/p/19orD
Bild : Der Bundeswettbewerb Fremdsprachen Wettbewerb 2013.Preisverleihung am 16 mai 2013 Hamburg Gymnasium Farmsen Hamburg . Titel: Der Bundeswettbewerb Fremdsprachen Wettbewerb 2013 : die Muttersprache ist ein Schatz" für effektive Integrationsarbeit Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn 2013 Schlagworte: Der Bundeswettbewerb Fremdsprachen Wettbewerb 2013
ምስል Azeb Tadesse Hahn

አንድ ሰው ማንነቱን ማለት ከመጣበት ወይም ከሚወለድበት ሀገር ፣ የዘር ሀረግ፣ ቤተሰብ ፣ ህብረተሰብ ፣ የሚወርሰውን እንደ ሐይማኖት ፣ሀገር ፣ባህል እና ቋንቋዎች ላሉ እሴቶች ማወቁ እና ማሳወቁ በሚኖርበት አዲስ ሀገር ምን ያህል ፋይዳ ይኖረዋል? የማንነትን መለያ ማወቅ በስብዕና ላይ የሚጫወተዉ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነዉ የሚሉንን ኢትዮጵያዊ አባት እና ልጅ የዛሪዉ እንግዳችን አድርገናል።

በጀርመን ተወልዳ ያደገችዉ የ 13 ዓመትዋ ታዳጊ ወጣት ትዝታ ጊቲ ገላዬ ትባላለች። ትዝታ ትምህርቷን በአብዛኛዉ በጀርመንኛ ቋንቋ ብቻ ብትከታተልም አማርኛ ቋንቋን በቤተሰቦችዋ ብርታት በደንብ ለመናገርመብቃትዋን ነግራናለች፤ መናገር ብቻ ሳይሆን መፃፍና ማንበብም ትሞክራለች። ታዳጊዋ ወጣት ትዝታ በምትኖርበት ከተማ ሃንቡርግ ዉስጥ በተደረገ የስነ -ፅሁፍ ዉድድር ተካፍላ አንደኛ ወጥታ መሸለምዋም እዚህ በጀርመን ሀገር ተነግሮላታል።

የትዝታ አባት ዶክተር ጌቲ ገላዬ፤ በሃንቡርግ ዩንቨርስቲ የአፍሪቃ እና የኢትዮጵያ ጥናቶች የትምህርት ክፍል መምህር ናቸዉ። ከሀገር ርቀዉ፤ በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሀገራቸዉን ቋንቋ ባህልና የማንነታቸዉን መለያ ለልጆቻቸዉ ማስተማራቸዉ፤ ልጆቹ በሚኖሩበት ሀገር፤ በሙሉ ስብዕና ፤በኩራት ኑሮአቸዉን እንዲገፉ፤ የሀገርንም ምንነት በኩራት መግለፅ እንዲችሉ፤ በትምህርታቸዉም ጠንካራ እንዲሆኑ እንዲቀጥሉ ይረዳቸዋል ሲሉ ከልምዳቸዉ አጫዉተዉናል፤ የለቱን እንግዶቻችን ሙሉ ቃለ-ምልልስ፤ የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ያድምጡ!

Schlepper fahren am 11.05.2013 beim Schlepperballett während des größten Hafenfests der Welt im Hafen von Hamburg vor den Landungsbrücken entlang. Vom 09. bis zum 12.05.2013 findet in Hamburg der 824. Hamburger Hafengeburtstag statt. Foto: Bodo Marks/dpa +++(c) dpa - Bildfunk+++ pixel
ምስል picture-alliance/dpa

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ