1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያሬዳዊ ዜማ በጀርመኑ መድረክ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2005

ባለፈዉ ሳምንት የራድዮ ጣብያችን ባለበት ቦን ከተማ አቅራብያ በሚገኘዉ ኮለኝ ከተማ ባሉ የተለያዩ የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት፤ ከዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ከያንያን የአገሮቻቸዉን ጥንታዊ የሙዚቃ ስልቶችን አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/19ANq
Auf dem Bild: Der Saint Yared Choir aus Äthiopien während der Romanischen nacht am 12.7.2013 in St. Maria Kapitol in Köln. Foto: Azeb Tadesse Hahn / DW
ምስል DW/A.Tadesse-Hahn

በዚህ ዝግጅት ላይ ያሪዳዊ ዜማን ያቀረቡ ኢትዮጵያዉያንም ተካፋይ ነበሩ፤ በኮለኝ ከተማ ባለፈዉ ሳምንት ዓርብ በቀረበዉ ዝግጅትን ቃኝተን በዕለቱ መሰናዶአችን ልናካፍላችሁ ይዘናል፤

Auf dem Bild: Alemu Aga- Begena spielt die König David Harfe während der Romanischen Nacht am 12.7.2013 in St. Maria Kapitol in Köln. Foto: Azeb Tadesse Hahn / DW
ምስል DW/A.Tadesse-Hahn

«የሮማዉ በጋ በኮሎኝ» የተሰኘዉ እና ከ25 ዓመት በፊት የጀመረዉ የሙዚቃ ድግስ በኮሎኝ ከተማ በሚገኙት 12 የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት አቅርበዉ ነበር። አንጌሎስ/ ዲያቤሎስ --በጥሬ ትርጉሙ ፣ መላእክትና ዲያብሎስ በሚል ስያሜ የተካሄደዉ የሙዚቃ ምሽት ላይ በዓለም ዙሪያ ፣ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ የጥንታዊና ዘመናዊ ሙዚቃ አዋቂዎች፤ ተካፋይ ነበሩ። በመካከለኛዉ ዘመን እና ከዛም ለዘመናዊ ሥልጣኔ የመነቃቃት ሂደት በተጀመረበት ዘመን የተከሠተ የሙዚቃ ስልቶችን ማለት የባሮክ ሙዚቃ፤ የረቂቅ ሙዚቃ እና የጃዝ ሙዚቃ የመሳሰሉትን አቅርበዉ ተቀባይነትን አግኝተዉ እንደነበር ይታወሳል።

ባለፈዉ ዓርብ ምሽት በኮለኝ ማዕከል በሚገኘዉ ቅድስት ማሪያ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተለያዩ መንፈሳዊና ፍልስፍና ይዘት ያላቸዉ ባህላዊ ሙዚቃዎች ቀርበዋል። በቅድስት ማርያ ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ የተካሄደዉ ዝግጅት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት እስከ ለሊቱ ስምንት ሰዓት የዘለቀ ነበር። የጀርመን፤ የቡልጋርያ ጥንታዊ የረቂቅ ሙዚቃ ቅላጺ በጥንታዊ እና ዘመናዊ ሙዚቃ ተቀናብረዉ የቀረቡበት መዘምራንን ያቀፈ ነበር። በዚሁ እስከ ሌሊቱ ስምንት ሰዓት በዘለቀዉ የሙዚቃ መድረክ ላይ የዳዊት ዝማሬን ያቀረቡ የያሬድ መዘምራን አባላት ተካፋይ ነበሩ።

ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ ሃገራት የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃ መሣርያን በሚጫወቱ በተለያዪ የዓለም ቋንቋዎች የሚያዜሙ ከያኒዎችን ወደ ጀርመን በመጋበዛቸዉ የሚታወቁት በጀርመን ታዋቂ የሆኑት ሙዚቀኛ ፒት ቡደ «የሮማዉ በጋ በኮለኝ» በተሰኘዉ የዓለም ጥንታዊ የረቂቅ ሙዚቃ ድግስ ላይ ተገኝተዋል። ፒት በዚህ ለሙዚቃ ድግስ አዘጋጆች ከኢትዮጵያ የጥንታዊዉን የያሬድን ዜማ ቢያስደምጡ ጥሩ መሆኑን ምክር ሰጥተዉ የያሬድ ዝማሪ እና የበገና ዜማ በድግሱ ላይ መቅረቡን ነግረዉናል ። ፒት ቡደ በገና አሉ ፤

Alemu Aga- Begena König David Harfe
ምስል DW/A.Tadesse-Hahn

«ለባህላዊ ሙዚቃ ከፍተኛ ፍቅር አለኝ። ያንን ስል የተለያዩ አገራት ባህላዊ ሙዚቃ ማለቴ ነዉ። አብዛኛዉን ግዜ ወደ ኢትዮጵያ በመሄዴ ብዙ ነገሮችን አይቻለሁ፤ እንደ አዲስም ተዋዉቄአለሁ። የዳዊት በገና ግን ልዩ ሆኖ ያገኘሁት፤ በጣም አስገራሚ የሆነ የሙዚቃ መሳርያ ነዉ። በገና የዘመናት ታሪክ መግለጫ ጥንታዊ መሳርያ ነዉ። የበገና ሙዚቃን ሲሰሙ፤ ራሱን መሳርያዉን ሲያዩ ሙዚቃ ከ2000 እና ከ 3000 ዓመት በፊት ምን አይነት ቅላጼ እንደነበረዉ መረዳት ይቻላል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሌላዉ ዓለምም የሙዚቃ ዓይነቱ ምን እንደሚመስል ገላጭ ነዉ። ከበገና የሚደመጠዉ ዜማ፤ ጥንታዊና እጅግ ንጹህ ሙዚቃ ነዉ። የበገና ቅላጼ ከሚዜመዉ ዜማ ጋር ሲደመጥ፤ በተለይ ደግሞ በድሮ ግዜ በአዉሮጳ የነበረዉ አይነት ሙዚቃ በመሆኑ፤ በአሁኑ ዘመን ይህን አይነቱን ዜማ ማግኘትና ማድመጡ እጅግ አስደሳች ነዉ»

በአውሮጳ ሙዚቃ ገናና ስም ያላቸው የሙዚቃ ቀማሪውች ከመፈጠራቸው ከሺህ ዓመታት ቀደም ብሎ የተፈጠረዉ የሙዚቃ ሊቅ የቅዱስ ያሪድ ዜማን ከኢትዮጵያ የመጡት የቅዱስ ያሪድ መዘምራን እጅግ ሰፊና ረጅም ጣሪያ ባለዉ በኮለኙ የቅድስት ማርያ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን መድረክ ሲዜሙ እጅግ ዉበትን አግራሞትን አጎናጽፈዋል የሙዚቃ ድግሱን ለማድመጥ በቦታዉ ላይ የነበሩት እድምተኞችም ደስታና አግራሞታቸዉን በጭብጨባ ገልጸዋል፤ ያሪዳዊ ዜማን ያቀረቡት ደብተራዎች ሲሉም ነዉ ያወቋቸዉ፤

Auf dem Bild: Der Saint Yared Choir aus Äthiopien mit Pitt Bude während der Romanischen Nacht am 12.7.2013 in St. Maria Kapitol in Köln. Foto: Azeb Tadesse Hahn / DW
ምስል DW/A.Tadesse-Hahn

በአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምርያ ሃላፊ እንደሆኑ የነገሩን መምህር እንቁ ባህሪ ተከስተ፤ ያሪዳዊ ዜማን በአዉሮጳ ለማቅረብ አላማ አድርገን የመጣነዉ ቅዱስ ያሪድን ለማስተዋወቅና በዓለም ቅርስነት ለመያዝ ነዉ።

የቅዱስ ያሪድ ታሪክ በጀርመንኛ እና በእንጊሊዘኛ ጽሁፍ ታትሞ፤ የበገና ምንነት እና የኢትዮጵያ ታሪክ በጥቂቱ የሰፈረበት መግለጫ አነስ ያለች መጽሄት፤ ገና የሙዚቃ ድግሱ ሳይጀምር ተመልካቹ ወደ ቤተ-ክርስትያኑ ወደተዘጋጀለት ቦታ ሲገባ ይዞ ነበር የገባዉ፤ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ ለጀርመናዉያን አዲስ እንግዳ አልነበሩም፤ ገና በገናቸዉን ይዘዉ ወደ መድረኩ ሲቀርቡ ተመልካቹ በሞቀ ጭብጨባ ተቀበላቸዉ፤

ከዝያም የዜማቸዉን ፍቺ አጠር ባለ መልኩ በእንግሊዘኛ ተርጉመዉ በገና ድርደራቸዉን ቀጠሉ ፤

ጀርመናዉያኑ የበገና ድርደራዉን አይተዉ ሲደመሙ ሲደሰቱ ላየ፤ ለተለያየ ባህልን የማወቅ ጉጉታቸዉ፤ አልፎ ተርፎም መዉደዳቸዉን ማየቱ በራሱ የሚሰጠዉ ደስታ ለመግለጽ ትንሽ ያዳግታል፤ አሁንም በጭብጨባ ምስጋናቸዉን አቀረቡ አለሙ አጋም በገና ድርደራቸዉን

መጋቤ ስብሃት ዓለሙ አጋ በዚህ ዝግጅታችን ሲቀርቡ የመጀመሪያቸዉ ባይሆንም ስለ ስም ማዕረጋቸዉ ግን አልጠየቅናቸዉም መጋቤ ስብሃት አሉ እዉቁ በገና ደርዳሪ አለሙ አጋ ፤ ምስጋናን በማቅረቤ ምስጋናን በመመገቤ ነዉ ሲሉ መልሰዉልናል። ያሪዳዊ ዜማን በኮለኙ ቅድስት ማርያ ካቶሊካዊ ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጥንታዊ ፍልስፍናን የሚያንፀባርቅ ፤ የረቂቅ ሙዚቃና ባህላዊ የቤተ-ክርስትያን በቀረበበት መድረክ ላይ ካቀረቡት ቡድኖች መካከል ሊቀ ጠበብት ገብረ መስቀል ሙሉም ይገኙበታል። ዝማሜ አቋቋም ወረብ እና ሽብሸባን ዉብ የሆነዉን ባህላዊ አልባሳት አድርገዉ በኮለኝ ከተማ ለጀርመናዉያን ያቀረቡት፤ የቅዱስ ያሪድ መዘምራን፤ ወደ አገር ቤት ከመመለሳቸዉ በፊት፤ ለራድዮ ጣቢያችን አንድ መቋሚያ እና አንድ ጸናጽል አበርክተዋል፤ በምስጋና ተቀብለን፤ የዝግጅት ክፍላችን የመታሰብያ እቃ ማስቀመጫ ማህደር ዉስጥ አኑረናል፤ እናመሰግናለን። መጋቤ ስብሃት አለሙ አጋ ላደረጉልን ትብብርም ምሥጋናችን እናቀርባለን። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ

Auf dem Bild: Der Saint Yared Choir aus Äthiopien während der Romanischen nacht am 12.7.2013 in St. Maria Kapitol in Köln. Foto: Azeb Tadesse Hahn / DW
ምስል DW/A.Tadesse-Hahn

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ