1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮጳና ጀርመን፣ 2024 የምርጫ ዓመት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 6 2016

የዴሞክራሲያዊ ስራት በሰፍነባቸው አገሮች ደሞክራሲያዊ ምርጫ፤ ህዝብ፤ መንግስታትን ለመለወጥ፤ መሪዎቹን ለመሾም ወይም ለመሻር የሚጠቀምበት፤ተቃውሞ ድጋፉን በማንጸባረቅ ስሜቱን የሚገልጽበትና ሉዑላዊዊነቱን የሚያረጋግጥበት አይነተኛ መሳሪያ ነው።

https://p.dw.com/p/4fquK
ግንቦት ማብቂያ ላይ ለሚደረገዉ የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ምርጫ በአባል ሐገራት ዉስጥ የምረጡኝ ዘመቻ ተጀምሯል
ለአዉሮጳ ሕብረት የምክር ቤት አባላት ምርጫ ክርክር ከሚደረግባቸዉ የምርጫ ዘመቻዎች አንዱ።ቡካሬስት-ሩሜንያምስል Cristian Ștefănescu/DW

አዉሮጳና ጀርመን፣ 2024 የምርጫ ዓመት

 

ዘንድሮ የምርጫ አመት ነው ማለት ይቻላል። በዚህ የጎሮጎሲያውያን አመት ብቻ በአለም ከ60 በላይ የብሂራዊ ምርጫዎች እንደሚካሄዱ ነው የሚጠቀሰው።  በዓለም ትልቅ የህዝብ ቁጥር የተሳተፈበትና ለቀናት የዘለቀ የህንድ ምርጫ ተካሂዷል። የአለም ትልቋ ሀያል አገር አሜሪካ ምርጫም በዚሁ አመት ነው የሚካሄደው። እዚህ አውሮፓም 450 ሚሊዮን የ27ቱ ያኣውሮፓ ህብረት አባል አገሮች ዜጎች የሚሳተፉበት ያውሮፓ ፓርላማ አባላት ምርጫ ዋዜም ላይ ነው የምንገኘው።  አንዳንድ የህብረቱ አባል አገሮች ቤልጅየምን ጨምሮ የብሄራዊና የአካባቢ ምርጫዎቻቸውንም በዚሁ ያውሮፓ ፓርላማ ምርጫ በሚካሄድበት ግዜ ደርበው ያካሂዳሉ።

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የህዝብ ልዕልና መገለጫ

የዴሞክራሲያዊ ስራት በሰፍነባቸው አገሮች ደሞክራሲያዊ ምርጫ፤ ህዝብ፤ መንግስታትን ለመለወጥ፤ መሪዎቹን ለመሾም ወይም ለመሻር የሚጠቀምበት፤ ተቃውሞ ድጋፉን በማንጸባረቅ  ስሜቱን የሚገልጽበትና ሉዑላዊዊነቱን  የሚያረጋግጥበት አይነተኛ መሳሪያ ነው።  በዕርግጥ የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች ዜጎች  እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ  ለብሄራዊና አክባቢያዊ ምርጫዎች እንጂ ለአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ብዙም ትኩረት አይሰጡም ነበር።

ዋና  መቀመጫቸውን ብራስልስና ስትራስቡርግ ያደረጉት የህብረቱ ተቁማትና ፓርላማው ከህዝቡ የራቁና በዜጎች የዕለት ተለት ህይወት ላይ ተጽኖ የሌላቸው ተደርጎ ይወሰድ እንድነበር ነው የሚታወቀው። ይህ ግን ባሁኑ ወቅት በእጅጉ እንደተለወጠ ነው የሚነገረው። ፓርላማው በህብረቱ አባል አገሮች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህጎችን የሚያወጣ፤ በጀት የሚያጸድቅና የህብረቱን ተቋማት መሪዎች ማለት፤ የኮሚሽኑንና የካውንስሉን ፕሬዝደንቶችና የህብረቱን የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሹመቶች የሚያጸድቅና የሚቆጣጠርም ነው ።። በህብረቱ ዜጎች የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊና፤ የደህንነት ፖሊስዎች ላይ ጉልህ ሚና ያለው መሆኑ እየታወቀ በመምጣቱ፤ የህዝቡ አስተያየት እንደተለወጠና በተለይ በዚህ አመት ምርጫ ደግሞ ከመቼውም ግዜ ይበልጥ የህዝቡ ተሳትፎ እንደሚጨምር ከኮሚሽኑ የሚወጡ የህዝብ አስተያየት መመዘኛዎች ያስረዳሉ።፡ ከአምስት አመት  በፊት እ እ እ 2019 አም  50.2  ከመቶ  የነበረው የመራጩ ህዝብ ብዛት ዘንድሮ 67 ከመቶ እንደሚሆን ነው የአስተያየት መመዘኛ ባለሙያዎች የሚናገሩት።   በፓሪስ የካንታር ፐብሊክ የሀዝብ አስተያየት መመዘኛ ቢሮ ተመራማሪ የሆኑት ሚስተር ስቴዋርት ቻው ይህንኑ በጥናታቸው እንዳረጋገጡ ይገልጻሉ: “ እኛ ባሰባሰብነው መረጃና ባክሄድነው ጥናት 71 ከመቶ የሚሆኑት አውርፓውያን ህብረቱ በእለት ተለት ህይወታቸው ላይ ተጽኖ ያለው መሆኑን ያምናሉ። በዚህ አመትም ከመራጩ ህዝብ በአማካይ  67 ከመቶው በምርጫው ይሳተፋል ብለው እንደሚያምኑ የጥናት ግኝታቸውን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል።።

በዘንድሮዉ ምርጫ ዕድሜያቸዉ 16 ዓመት የሆነ ወጣቶች ድምፅ መስጠት ይችላሉ
በዘንድሮዉ የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ምርጫ ድምጻቸዉን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጡ የጀርመን ወጣቶችምስል EU

የምርጫው ሂደትና አፈጻጸም፤ የምክርቤት አባላት ብዛትና ድልድሉ

 

በአውሮፓ ለብሄራዊ ወይም አካባቢያዊ ምርጫዎች የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎችን በማቅረብና በማወዳደር እንደሚሳተፉ ህሉ፤ ለአውሮፓ ፓርላማም በያአገሮቹ ያሉት ፓርቲዎች ናቸው እጩዎቻቸውን የሚያወዳድሩትና አስመርጠው የሚልኩት። የአገሩ ፓርቲዎች ግን ከሌሎች  አባል አገሮች ተመሳሳይ አላማ ከሚያራምዱ ፓርቲዎች ጋር በመቀናጀትና አብሮ በምስራት ነው በአውርፓ ደርጃ ምርጫ የሚወዳደሩትና ከተመረጡም የሚሰሩት። በዚም መሰረት የመሀል ቀኝ ፓርቲዎቹ የአውሮፓ ህዝቦች ፓርቲ ፣  በእንግሊዥኛ ምህጻሩ EPP፣ የመሀል ግራዎቹ ፓርቲዎች የአውሮፓ ሶሻሊስቶችና  ዴሞክራቶች  በእንግሊዝኛ ምህጻሩ S & D፣ የሊብራል ፓርቲ ስብስቦች፤ ቀኞቹ፣ የአውሮፓ ወግ አጥባቂዎች፤ የማንነትና ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ፤ የአረንጉዴ ፓርቲዎችና የግራዎቹ ሃይሎች እንዲሁም ሌሎች ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ያልተቀናጁ ፓርቲዎች ጭምር በየአገሮቻቸውና  የምርጫ ጣቢያቸው ይወዳደራሉ። ከጠቅላላው  720 የአውሮፓ ፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ  ለየአገሮቹ የተደለደለው  እንደ ህዝባቸው ብዛት ሲሆን፤ ለምሳሌም ጀርመን 96 ፈርንሳይ 81 መቀመጫዎች ናቸው ያሏቸው። የሀዝብ ብዛታቸው ትንሽ የሆኑ ለምሳሌ እንደ ሉክዘምበርግና ማልታ፤ ቢይንስ ስድስት ስድስት መቀመጫዎች እንዲኖራቸው ተደርጎ ነው ድልድሉ የተሰራው።

የዘንድሮው ምርጫ ልዩና ተጠባቂ የሆነባቸው ምክኒያቶች  

እያንዳንዱ ምርጫ  በራሱ የሶሻል ኢኮኖሚና ፖለቲካዊ አጀንዳዎችና ተግዳሮቶች ውስጥ የሚካሄድ  መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም የዘንድሮው ምርጫ ግን የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች መፍትሄ በሚሹበት፤ የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት መላው የህብረቱን ዜጎች ባስመረረበት ወቅት፤ ፈላሳያንና ስደተኖች የደህንነት ስጋት መሆናቸው በሰፊው እየተነገረ ባለበት ግዜ የሚካሄድ በመሆኑ የተለየ እንደሆነ ተደርጎ ነው የተወሰደው።፡ ከሁሉም በላይ ግን ዛሬ በውሮፓ የህብረቱን ነባር እመንቶችና እሴቶች ጭምር ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ የቀኝ አክራሪና ህዝበኛ የፖለቲክ ፓርቲዎች ባንሰራሩበትና በአንዳንድ አባል አገራትም መንግስት እስክመሆን በደረሱበት ግዜ የሚካሄድ መሆኑ ምርጫውን በእውነትም የተለየና የሚጠበቅም  አድርጎታል።

በእስካሁኑ የህብረቱ ታሪክ ህብረቱን የሚመሩት አፍቃሪ አውሮፓ ህብረት የሆኑት የመሀል ቀኝና  ግራ ፕርቲዎች ጥምረት ከአርንጉዴዎቹና ሊበራሎቹ ጋር በመተባበር ሲሆን፤  ይህ ምርጫ ግን  ይህን ነባር የፖለቲክ ጥምረትና የሀይል አሰላለፍ ሳይቅይረው እንደማይቀር ነው በሰፊው የሚነገረው። በነባሮቹና አዲሶቹ አክራሪና ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች መካከል ሰፊ ልዩነቶች እንዳሉ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ሁሉም ግን በአንድ አጀንዳ-ከዩክሬን ጎን በመቆምና በመደገፍ ጥያቄ ላይ ምናልባትም ከህንጋሪ ገዥ ፓርቲ በስተቀር  ተመሳሳይ አቋም አላቸው ነው የሚባለው ።  ከኢሮ አሺያ ግሩፕ ሚስተር ያን ቴቻው እንደሚሉት በዚህ በኩል ያውሮፓ ፓርቲዎች አንድነት የሚገርም ነው፤።፡ “ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁንም ድረስ ለዩክሬን  ሊሰጥ በሚገባው እርዳታ ያውሮፓ ህብረት መንግስታትና ፓርቲዎች ምናልባትም ከአንድ ፓርቲ በስተቀር በአንድ ላይ ከዩክሬን ጎን  እንደቆሙ ናቸው” በማለት በዚህ ምርጫ ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ እንዲቆም የሚፈልጉ ፓርቲዎች ሊኖሩ ቢችሉ እንኳ፤ ጎልተው የሚወጡ እንደማይሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ሆኖም ግን ይህም ቢሆን ጦርነቱ ከተራዘመና የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ ከሄደ፤  ከሁሉም በላይ ደግሞ  የአሚሪካው  የምርጫ ውጤት የአሜርካንን የዩክሬን ድጋፍ እንዳለ እንዲቀጥል የማይስችል ከሆነ፤ ያውሮፓ የዩክሬን ድጋፍም ጥያቄ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ነው የሚገመተው።

በዘንድሮዉ የአዉሮጳ ሕብረት የምክር ቤት ምርጫ የሚወዳደሩ የፈረንሳይ ዕጩዎች
ለአዉሮጳ ሕብረት የምክር ቤት አባላት ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎች በከፊል-ፈረንሳይምስል Hans Lucas/AFP/Getty Images

የተወዳዳሪ ፓርቲዎች የልዩነት አጀንዳዎች

በሌሎቹ አጀንዳዎች  ላይ ግን ግን የፓርቲዎቹ ልዩነት መሰረታዊ እንደሆነና በህብረቱ ፕሊሲዎችና ፕሮግርሞች ፈጻጸም ላይ ከፍተኝ ችግር ሊስተዋል እንደሚችል ነው  ነው ከወዲሁ እየተነገረ ያለው። ለምሳሌ የህብረቱ አይነተኛ ችግርና አጀንዳ ሆኖ በዘለቀው የፈላስያንና ስደተኖች ጉዳይ፤ የመሀል ቀኙ የአውሮፓ ህዝብ ፓርቲ ኢፒፒ፤ ደንበር በማጥበቅና  ከሶስተኛ አገሮች ጋር ስምምነት በማድረግ ስደተኖችን መከላከል የሚል ፕሮግራም ያለው ሲሆን፤ የመሀል ግራው ወይም ሶሻሊስቶቹ ፓርቲ ደግሞ ስምምነቱ ፍትሃዊና ሰባዊ ሊሆን ይገባዋል በማለት ይክራከራል። የጣሊያን ወንድማማቾችና የፖላንድ የህግና ስራት ፕርቲዎች የሚገኙበት የወግ አጥባቂዎቹ ስብስብ ደግሞ፤ ስደተኖችን የመቀበል ግዴታ ሊኖር እንደማይገባና ፈላሲያኑን የሶስተኛ አገሮች ጋር በመዋዋል እንዲገቱና ተመልሰውም እንዲላኩ የሚያስችል ስራ መሰራት እንዳለበት ያምናል ። ለጀርመን አማራጭ ፓርቲና በወይዘሮ ሌፐን የሚመራው የፈርንሳይ  አክራሪ ብሄረተኝ ፓርቲ ያሉበት  የማንነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ደግሞ፤ ከዚህም በበለጠ ስደተኛ ጠልና በአባል አገሮቹ ላሉት ችግሮች ዋናው ምክኒያት  ከፈላስያንና ስደተኖች ወደ አውርፓ መግባት ጋር የተያያዘ እንደሆነ የሚያምን ነው።፡

የአውሮፓ ቀኝ አክራሪ ፓርቲዎች የጋራ እምነቶችና አቋሞች

በዚህ ምርጫ ከፍተኛ ድምጽ አግንተው ባውሮፓ ህብረት ነባር አሰራር ላይ ተግዳሮት ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚባሉት የቀኝ አክራሪ አሀይሎችን በካርሊ ዩንቨርስቲ ፕሮፊሰር የሆኑት ሎረንዞ ካስቴሊያኒ በተለይ ሶስት የጋራ መሰረታዊ  አቁሞችና እምነቶች እንዳሏቸው ያስረዳሉ፤ “ የመጀመሪያው ጸረ ስደተኛና ፈላስያን መሆናቸው ነው። ይህ የሁሉም የቀኝ አክራሪና ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች የጋራ አቋም ነው፤፡ ሌላው የአውሮፓ ህብረትን አንድነት በሙሉ ልብ ያለመደገፍ ወይም ኢሮ ስኬፕቲክ መሆናቸው ነው ። በዚህ ላይ ሁሉም የህብረቱን የተፋጠነ የአንድነት ጉዞ አይፈልጉም። ሶስተኛው፤ ሁሉም ተራውን ህዝብ የምንወክልና  ስሜቱን የምንጋራ ነን ባዮች መሆናቸው ነው በማለት የአውሮፓ አክራሪና ወግ አጥባቂ ፓርቲዎችን የጋራ እምነትና አቋም ግልጽ አድረገዋል።
በብራስልስ ነጻ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፈሰር የሆኑት ዴቨ ሲንዳርዴት በበኩላቸው በተለይ ያውሮፓ የቀኝ አክርሪዎች የተስብሰቡበት የማንነትና ዴሞክርሲ ስብሰብ የበለጠ አክራሪና ቀኝም  እንደሆነ ነው የሚናገሩት፤ “ባጠቃላይ በማንነትን ዴሞክራሲ ቡድን ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች በጣም አክራሪ የቀኝ ሀይሎች ናቸው። የአውሮፓ ህብረትንም እንደተቋም የሚቃወሙ ናቸው በማለት የወግ አጥባቂዎቹ ስብስብሰብ ግን፤ ህብረቱን በደፈናው ከመቃወም ባለፈ ከህብረቱ ተቋማት ጋር እንደሚሰራም የጣሊያኑን የወይዘሮ ሜሎኒን የወንድማማቾች ፓርቲ ለአብነት በመጥቀስ አሰረድተዋል።

ጀርመን ዉስጥ ለአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት አባልነት የሚደረገዉ የምርጫ ዘመቻ በከፊል
ለአዉሮጳ ሕብረት የምክር ቤት አባላት ምርጫ ጀርመን ዉስጥ ከሚደረጉ የምርጫ ዘመቻዎች በከፊልምስል JOHN MACDOUGALL/AFP/Getty Images

 የምርጫዉ ውጤት የአውሮፓ ህብረትን ወዴት ይመራው ይሆን?

የምርጫ ዉጤት ትንቢያዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ፤  በስኔው ምርጫ ውጤት በአውሮፓ ፓርላማ ከፍተኛውን መቀመጫ ይዞ የቆየው የመሀል ቀኙ ያውሮፓ ህዝቦች ፓርቲ፤ በርካታ መቀመጫዎችን የሚያጣ ቢሆንም፤ አሁንም ግን ትልቁ ፓርቲ ሆኖ እንደሚቀጥልና ላውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳትነት እጩ አድርጎ ያቀረባቸውን ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴርሌይንን በድጋሜ ማስመረጡ እንደማይቀር ነው። የሶሻሊሲቶቹ ፓርቲ ከዚህ ቀደም የነበረውን የመቀመጫ ብዛት በመያዝ ሁለተኛ ሆኖ እንደሚቀጥል የሚገመት ሲሆን፤ የሊበራሎቹ ፓርቲ ግን ብዙ መቀመጫዎችን እንደሚያጣና የሶስተኛነት  ቦታውንም ባዲሶቹ የቀኝ አክራሪ ፓቲዎች ስብሰብ በማንነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ወይም በአውሮፓ የወግ  አጥባቂዎች ፓርቲ ሊነጠቅ እንደሚችል ተገምቷል። ይህ ውጤት በፓርላምው የነበረውን የመሀል ቀኝና ግራ ፓርቲዎች  ጥምረት እንዳለ እንዲቀጥል ሊያደርግ ቢችል እንኳ፤ በአጀንዳዎችና ፖሊሲዎች  አተገባበርና ላይ ግን ለውጥ እንደሚኖር ነው የሚታመነው። በዚህም መሰረት ከመጭው ምርጫ በኋላና በሚቀጥሉት አምስት አመታት  ህብረቱ በተለይ በስደተኖች አጀንዳ ላይ የክረረና የጠበቀ እርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል እየተባለ ነው።  ባየር ለውጥ አጀንዳዎችም የአረንጉዴዎቹ ፓርቲዎች እየገፉት ባለው ልክ ሳይሆን ቀስ ያለና የኢኮኖሚ ጫናዎችን ያገናዘቡ እርምጃዎች ሊወሰዱና ታቅደው የነበሩ የአየር ለውጥ አጀንዳዎችም እንዲዘገዩ ሊደረግ ይችልይሆናል። ያውሮፓ ህብረትን ለማጠናከርና የህብረቱን አሰራርና ፖሊስዎች ለማዋሀድ የሚደረገው ጥረትም አዝጋሚ ሊሆን  እንደሚችልና በአጠቃላይም የዘንድሮው የአውሮፓ ምርጫ ውጤት በመጪዎቹ  አምስት አመታት ህብረቱ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ወደ ቀኝ  ያደላ እንዲሆን ሊያደርገው እንደሚችል ነው የሚታመነው።፡
ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ